Fana: At a Speed of Life!

ዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም በ2021 የዓለም ኢኮኖሚ እንደሚያገግም አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 29፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም በፈረንጆቹ 2021 የዓለም ኢኮኖሚ እንደሚያገግም ይፋ ባደረገው አዲስ ሪፖርቱ አስታወቀ፡፡

ተቋሙ በሪፖርቱ የዓለም ኢኮኖሚ በ2021 የ6 በመቶ እድገት እንደሚያስመዘግብ ነው የገለጸው፡፡

ይህም በጥር ወር ከተተነበየው የ0 ነጥብ 5 በመቶ  አሳይቷል፡፡

ተቋሙ በሪፖርቱ በፈረንጆቹ 2022 የ4 ነጥብ 4 በመቶ እንዲሁም በ2026 የ3 ነጥብ 3 በመቶ ዕድገት እንደሚጠበቅም በትንበያው አስቀምጧል፡፡

በፈረንጆቹ 2020 የዓለም ኢኮኖሚ በኮቪድ19 ወረርሽኝ ምክንያት ወደ ነጌቲቨ 3 ነጥብ 5 በመቶ አሽቆልቁሎ እንደነበርም በሪፖርቱ ጠቅሷል፡፡

በጥቅሉ የበለጸጉት ሃገራት በ5 ነጥብ 1 በመቶ እንደሚያድጉ የተነበየው ባንኩ የአሜሪካ ኢኮኖሚ በ6 ነጥብ 4 በመቶ እንደሚያድግ ይጠበቃልም ነው ያለው፡፡

በማደግ ላይ የሚገኙ ሃገራት ጥቅል የ2021 እድገት 6 ነጥብ 7 በመቶ ይሆናል ነው የተባለው፡፡

ከእነዚህ ሃገራት መካከልም ህንድ በላቀ ሁኔታ የ12 ነጥብ 5 በመቶ እድገት እንደምታስመዘግብ ነው ይፋ ያደረገው፡፡

ከሰሃራ በታች ያሉት ሃገራት የ3 ነጥብ 4 በመቶ እድገት እንደሚያስመዘግቡ የጠቀሰው ትንበያው፥ ኢትዮጵያ በተያዘው የፈረንጆቹ አመት በ2 በመቶ እንዲሁም በ2022 የ8 ነጥብ 7 በመቶ እንደምታስመዘግብም ነው ያመላከተው፡፡

ከሰሃራ በታች የሚገኙ ሀገራት ባለፈው የፈረንጆቹ አመት 10 ነጥብ 8 በመቶ የነበረው የዋጋ ግሽበት በ2021 ወደ 9 ነጥብ 8 በመቶ እንሚወርድ ነው የገለጸው፡፡

በኢትዮጵያ የዋጋ ግሽበቱ ባለፈው የፈረንጆቹ አመት 20 ነጥብ 4 እንደነበር ጠቅሶ በ2021 ትንበያው መሻሻል በማሳየት ወደ 13 ነጥብ 1 እንሚወርድ ነው ይፋ ያደረገው፡፡

በዚምባብዌ የዋጋ ግሽበቱ የከፋ ሲሆን በ2020 ከነበረበት 557 ነጥብ 2 በመቶ በ2021 ወደ 99 ነጥብ 3 በመቶ እንደሚወርድ ይጠበቃል ብሏል፡፡

በሱዳን በባለፈው የፈረንጆቹ አመት 163 ነጥብ 3 በመቶ የነበረው የዋጋ ግሽበት ጭማሪ በማሳየት 197 ነጥብ 1 በመቶ እንደሚሆንም ተቋሙ ትንበያውን አስቀምጧል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.