Fana: At a Speed of Life!

ዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም (አይ ኤም ኤፍ) ለኢትዮጵያ የ2 ነጥብ 9 ቢሊየን ዶላር ድጋፍ አፀደቀ

ዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም ሥራ አስፈፃሚ ቦርድ ያጸደቀው ይህ ድጋፍ የኢትዮጵያን ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ ፕሮግራም ለመደገፍ  የሚውል  መሆኑ ተገልጿል፡፡

የተገኘው ድጋፍም ኢትዮጵያ የጀመረችውን ሁለንተናዊ ለውጥ አጠናክሮ ለማስቀጠል ከፍተኛ አስተጽኦ አለው ተብሏል፡፡

የኢትዮጵያ የምታካሂደው ኢኮኖሚያዊ ማሻሻያ በበጀት ዓመቱ የውጭ ምንዛሬ እጥረትን ለመፍታት እና ተለዋዋጭ የሆነውን  የልውውጥ ተመን ስርዓት በማስተካከል ላይ ያተኩራል ተብሏል ፡፡

በሀገሪቱ ሥራ አጥ ለሆኑ ወጣቶች የስራ እድል ለመፍጠር፣ የግሉ ዘርፍ ኢንቨስትመንትን ለማበረታታት  ያግዛል፡፡

በተጨማሪም በድህነት ቅነሳ ፣ አስፈላጊ  ለሆኑ የመሰረተ ልማት ወጪዎች ፣የግሉን ዘርፍ ተሳትፎ ለማበረታታትና ለማሳደግ፣   በዝቅተኛ የገቢ ምንጭ ያሉ የህብረተሰብ ክፍሎችን ማዕከል ያደረገ የልማት ስራን ለማከናወን እና የገንዘብ ፖሊሲ ማዕቀፉን ዘመናዊ ለማድረግ ለማሻሻል እንደሚያግዝም የገንዘብ ተቋሙ ገልጿል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.