Fana: At a Speed of Life!

ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት መስፈርቶችን በፖሊስ የስልጠና ስርዓት ትምህርት ማካተት በሚቻልበት ሁኔታ ውይይት ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 18፣ 2012(ኤፍ.ቢ.ሲ) ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት መስፈርቶች በፖሊስ የስልጠና ስርዓት ትምህርት ውስጥ በሚካተቱበት ሁኔታ ላይ ውይይት መካሄዱን ዓለም አቀፉ የቀይ መስቀል ኮሚቴ አስታወቀ።

በውይይቱ ከኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ እና ከፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን የተውጣጡ ተወካዮች እንዲሁም የክልል ፖሊስ ማሰልጠኛ ተቋማት ሃላፊዎች ተሳትፈዋል።

ኮሚቴው የፖሊስ ስልጠና ስርዓተ ትምህርትን የበለጠ ለማሻሻል እና የዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት መስፈርቶችን ለፖሊስ አባላት ለማስተዋወቅ እና ለመተግበር የሚደረጉ ጥረቶችን እንደሚደግፍ አስታውቋል፡፡

በተጨማሪም ተሳታፊዎቹ በተዘጋጀው ረቂቅ የመግባቢያ ሰነድ ላይ መምከራቸውን ከኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

የመግባቢያ ሰነዱ በዓለም አቀፍ ቀይ መስቀል ኮሚቴ እና በፖሊስ የስልጠና ማዕከላት መካከል ያለውን የስራ ግንኙነት በማጠናከር ተቋማዊ እና ዘላቂ ያደርገዋል ተብሎ ይጠበቃል።

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.