Fana: At a Speed of Life!

ዓለም አቀፍ የቱሪዝም ቀን በዓልን ለማክበር የክልል ርዕሳነመስተዳድራን ጅግጅጋ ገብተዋል

አዲስ አበባ፣ መስከረም 17፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ)ዓለም አቀፍ የቱሪዝም ቀን በዓልን ለማክበር የክልል ርዕሳነመስተዳድራን ጅግጅጋ ከተማ ገብተዋል፡፡

የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ርስቱ ይርዳው፣ የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ፣ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር ዶክተር ሒሩት ካሳሁን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች ናቸው ወደ ጅግጅጋ ያመሩት፡፡

በዓሉ በኢትዮጵያ “ቱሪዝም ለገጠር ልማት” በሚል መሪ ሀሳብ ሃሳብ ነው በከተማዋ ይከበራል የተባለው፡፡

በዋናነት በሲፖዚየምና የቱሪስት መዳራሻ ስፍራዎችን በመጎብኘት እንደሚከበር ተነግሯል፡፡

ከዚህ በተጨማሪ በጅግጅጋ ከተማ ለሚገነባው የባህል ማዕከል የመሰረት ድንጋይ አስቀምጠዋል።

ከተማዋ በ2008 ዓ.ም 28ኛውን የዓለም ቱሪዝም ቀን በዓልን ማስተናገዷን የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል።

የዓለም የቱሪዝም ቀን በጅግጅጋ ከተማ ዛሬ ሲከበር ለ2ኛ ጊዜ መሆኑን ኢዜአ ዘግቧል።

ዛሬ እየተከበረ የሚገኘው የቱሪዝም ቀን በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ41ኛ፤ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ33ኛ ጊዜ መሆኑን መረጃዎች ያሳያሉ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.