Fana: At a Speed of Life!

ዘመቻው የተጀመረውን የነጻነት ትግል ለማሳካት ወሳኝነት አለው – ምሁራን

አዲስ አበባ፣ ህዳር 15፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የጠቅላይ ሚኒስትሩ ወደ ግንባር መዝመት የተጀመረውን የነጻነት ትግል ለማሳካትና የውሸት ፕሮፓጋንዳ ለማክሸፍ ወሳኝነት አለው ሲሉ የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ምሁራን ገለጹ።

የአመራሩ ጦር ግንባር ድረስ መዝመት ፣ በምዕራባውያን ሚዲያዎችና ተላላኪዎቻቸው አገር ለማፍረስ የሚካሄደውን ፕሮፓጋንዳ ለማምከንና ኢትዮጵያ ተገዳ የገባችበትን የህልውና ጦርነት ለዓለም ለማሳየት እንደሚያግዝም ነው ምሁራኑ ያስረዱት፡፡

የጠቅላይ ሚኒስትሩ ግንባር መዝመት በሁሉም መስክ የኢትዮጵያን አሸናፊነት የሚያፋጥንና የሚያረጋግጥ ብሎም በሠራዊቱና በየደረጃው በሚገኙ ዜጎች ውስጥ ከፍተኛ የሞራልና የተነሳሽነት ስሜት የሚፈጥር አጋጣሚ መሆኑንም ምሁራኑ አመላክተዋል፡፡

የጠቅላይ ሚኒስትሩ በግንባር መገኘት በጦርነት ሂደት ውስጥ ሊፈጠር የሚችልን ውጣ ውረድ የበዛባቸውን የቢሮክራሲ ሰንሰለቶች እልባት በመስጠት የእጅ አዙር የቅኝ አገዛዝ ጦርነቱን በፍጥነት ለማገባደድ ያግዛልም ነው ያሉት፡፡

የመሪዎቹ ቁርጠኝነትና አገር ወዳድነት በመላው አለም የተጀመረውን የ “ ይበቃል ዘመቻ ” በማቀጣጠል የኢትዮጵያ ዳያስፖራዎች በመላው ዓለም የጀመሩትን ህዝባዊ ሠላማዊ የተቃውሞ ሰልፍ ያጠናክራል፤ የፓን አፍሪካኒዝም ዳግም ውልደት በመላው ዓለም ጥቁር ህዝቦች ዘንድ እንዲቀጣጠል ያነቃቃል ሲሉም ያስረዳሉ ምሁራኑ፡፡

በምዕራባውያን ዘንድ ድንጋጤ የፈጠሩት ህዝባዊ ሰልፎች አሜሪካ በአፍሪካ ቀንድ ላይ የምትከተለው የተሳሳተ ፖሊሲ ዳግም እንዲትፈትሽ ያደርጋታል በማለት የሰልፉን አንድምታ አብራርተዋል፡፡

ኤምባሲዎቻችን ኢትዮጵያ የያዘችውን ታላቅ አፍሪካዊ እውነት ለዓለም በማሳወቅና በማስረዳት የተጣለባቸውን ታሪካዊ ኃላፊነት ይበልጥ መወጣት እንዳለባቸውም አሳስበዋል፡፡

ምሁራኑ የመሪው መዝመት ህዝባዊ ማዕበልን የሚፈጥርና ለህልውና መረጋገጥ እያካሄድን የሚገኘውን ጦርነት ከግብ ለማድረስ እንድሚያግዝም ነው የገለጹት።

የህዳሴ ግድቡን ዕውንነት ለማረጋገጥ ከማስቻሉም በላይ ኢትዮጵያ “የውሃ ኒውክለር” በመታጠቅ በአፍሪካ ቀንድና በምስራቅ አፍሪካ የነበራትን ታሪካዊ ቦታና ተሰሚነቷን እንድታረጋግጥ ያስችላታል ነው ያሉት ምሁራኑ፡፡

ምሁራኑ በገንዘብም ሆነ ጦር ግንባር ድረስ ሄዶ በመዝመት ወራሪውን አሸባሪ ቡድን ለመደምሰስ እና የኢትዮጵያን ልዕልና ለማረጋገጥ ያላቸውን ቁርጠኝነት መግለጻቸውን የዘገበው ኢዜአ ነው፡፡

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.