Fana: At a Speed of Life!

ዘማቾች ድል እንዲጎናጸፉ ለዘማች ቤተሰቦች የሚደረገውን ድጋፍ ማጠናከር ይገባል ተባለ

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 14 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ዘማቾች በሙሉ ልባቸው ድል እንዲጎናጸፉ ለዘማች ቤተሰቦች የሚያደርጉትን ድጋፍ አጠናክረው እንደሚቀጥሉ አርሶ አደሮችና መንግሥት ሠራተኞች ተናገሩ፡፡
አሸባሪው ወራሪ ኃይል በወረራቸው የአማራ እና የአፋር ክልሎች ንጹሃንን ገድሏል፤ ሃብት ንብረት ዘርፏል፤ መዝረፍ ያልቻለውን አውድሟል፡፡
በባሕር ዳር ዙሪያ የወራሚት ቀበሌ አርሶ አደር ምናለ መንገሻ እርሳቸውና ጎረቤቶቻቸው ከግል ሥራቸው አስቀድመው ለአገራቸው እና ለወገናቸው ክብር ሲሉ በግንባር እየተፋለሙ የሚገኙ ዘማቾችን ሰብል ሰብስበዋል፡፡
የተሰበሰበውን ሰብል ወደ ጎተራ ከማስገባት በተጨማሪ ሌሎች የግብርና ሥራዎችን በማከናወን ዘማቾች በድል እስከሚመለሱ ቤተሰቡን የመጠየቅ ፣ የመደገፍ እና የማበረታታት ተግባራቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉም ተናግረዋል።
 
ሌላው አርሶ አደር መሰንበት ሳልል ኢትዮጵያን ለማፍረስ የተነሳውን አሸባሪ ወራሪ ኃይልን ለመደምሰስ በግንባር የተሰለፉ ዘማች ቤተሰቦችን ከመንከባከብ ባለፈ የተፈናቀሉ ወገኖችን በማቋቋም አንድነታችንን የበለጠ እናሳያለን ብለዋል፡፡
ዘማቾች በሙሉ ልባቸው ድል እንዲጎናጸፉ ለዘማች ቤተሰቦች የሚያደርጉትን ድጋፍ አጠናክረው እንደሚቀጥሉም አስታውቀዋል፡፡
የጉምሩክ ባሕር ዳር ቅርንጫፍ ሠራተኞችም በወራሚት ቀበሌ ተገኝተው የዘማቾችን ሰብል ሰብስበዋል፡፡
 
ኢትዮጵያ እንዳትፈርስ በግንባር ጠላትን በመደምሰስ ላይ ያሉ ዘማች ቤተሰቦች የግብርና ሥራዎችም ሆነ ሌሎች ሁለተንናዊ ድጋፎችን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ መናገራቸውን አሚኮ ዘግቧል።
 
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.