Fana: At a Speed of Life!

ዝንብ ሲያሳድዱ ቤታቸው በእሳት የተቃጠለው አዛውንት

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 2፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ዝንብ ሲያሳድዱ የነበሩ አንድ አዛውንት ቤታቸው በከፊል በእሳት ተቃጥሏል።

ኑሯቸውን ፈረንሳይ ያደረጉት የ80 ዓመት አዛውንት አርብ እራት በመብላት ላይ እያሉ አንድ ዝንብ እየጮኸች አበሳጭታቸዋለች።

ዝምታን ያልመረጡት እኚህ ግለሰብ ታዲያ ዝንቦችን በኤሌክትሪክ አቃጥሎ የሚገድለውን የኤሌክትሪክ ወንፊት ለኩሰዋል ይላል የኒውስ ስካይ ዘገባ።

በዚህም ዝንቧን ለመያዝ ሲሞክሩ በአቅራቢያ የነበረውን የጋዝ ሲሊንደራቸውን ገለበጡት።

ከዚያም የጋዝ ሲሊንደሩ አፍስሶ ቤታቸው ውስጥ እሳት ተፈጥሯል ነው የተባለው።

የተነሳው እሳትም የአዛውንቱን ማድቤት፣ የዋና ቤቱን ጣሪያ አውድሟል የተባለ ሲሆን ቤቱ በአሁኑ ወቅት ለመኖር የማያስችል ነው ተብሏል።

ይሁን እንጂ አዛውንቱ እጃቸው የተወሰነ ቢቃጠልም እንደምንም ከአደጋው ማምለጥ መቻላቸው የተነገረ ሲሆን፥ በእሳት የተጎዳው ቤታቸውም በቤተሰባቸው ጥገና እየተደረገለት እንደሚገኝ ታውቋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.