Fana: At a Speed of Life!

የሀላባን የዘመን መለወጫ በዓል ምክንያት በማድረግ የሩጫ ውድድር ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ጥር 2፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የሀላባን የዘመን መለወጫ በዓል ምክንያት በማድረግ የ8 ኪሎ ሜትር የሩጫ ውድድር በሀላባ ቁሊቶ ከተማ ተካሄደ።

“ሴራችን ለሰላማችን” በሚል ሀሳብ በተካሄደው የሩጫ ውድድር ላይ የአካባቢው ነዋሪዎች ተሳትፈዋል።

ውድድሩን ያስጀመረችው አትሌት ፋንቱ ምጌሶ “ሰላም ለሁሉም ነገር መሠረት በመሆኑ የሀላባ ብሄር የዘመን መለወጫ በዓሉን ከሰላም ጋር በማስተሳሰር መከበሩ ልዩ ያደርገዋል” ብላለች።

በውድድሩ ከአንደኛ እስከ ሶስተኛ ለወጡ የገንዘብና የተሳትፎ የምስክር ወረቀት ሽልማት እንደተበረከተላቸው ከኢዜአ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

የሀላባ ብሄር ዘመን መለወጫ በዓል ዛሬና ነገ በተለያዩ ዝግጅቶች ይከበራል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.