Fana: At a Speed of Life!

የሀገርን ሰላም በማስፈን የዲሞክራሲ ግንባታ ሂደት ግቡን እንዲመታ የሴቶች ሚና የጎላ መሆኑ ተገለፀ

አዲስ አበባ ፣ ነሃሴ 17፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የሀገርን ሰላም በማስፈን የዲሞክራሲ ግንባታ ሂደት ግቡን እንዲመታ የሴቶች ሚና የጎላ መሆኑ ተገለፀ።

በሀገር ሰላምና በዲምክራሲ ግንባታ ዉስጥ የሴቶች ተሳትፎ በሚል መሪ ቃል በጅግጅጋ ከተማ የሴቶች ኮንፍረንስ ተካሄዷል።

በኮንፍረንሱ የሶማሌ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ሀላፊ ኢንጂነር መሀመድ ሻሌ÷ ከዚህ በፊት በነበሩ የአስተዳደር ስርዓቶች ውስጥ ሴቶች የነበራቸው ተሳትፎ ውስን መሆኑን አንስተው ።

አሁን ላይ የሁሉም መብት የተረጋገጠባት እና ሰላምና ዲሞክራሲ የሰፈነባት ሀገር ለመገንባት ሴቶችን በሰፊው ማሳተፍ ተገቢ መሆኑን ገልፀው ከዚህ በኃላ በክልሉ የሚከናወኑ የአስተዳደር ስራዎች ሴቶችን በተገቢው መንገድ ያሳተፉ እንደሚሆን አረጋግጠዋል።

የሶማሌ ክልል የመንግስት ኮሙኑኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ሀላፊ አቶ አሊ በደል በበኩላቸው ሴቶች ለሰላምና ዲሞክራሲ ግንባታ ብቻ ሳይሆን በተለያዩ ዘርፎች ለሚመዘገብ ስኬት ሚናቸው የጎላ ነው ብለዋል።

የውይይቱ ተሳታፊዎች በበኩላቸው መንግስት አሁን ላይ ሴቶችን በተገቢው መልኩ ለማሳተፍ የጀመረው እንቅስቃሴ የሚያበረታታ መሆኑን በመግለፅ በሀገሪቱ የሚፈለገውን ልማት ለማምጣትም ሴቶችን አሳታፊ ያደረገ የአስተዳደር ስርዓት መዘርጋት እንደሚገባ ማንሳታቸውን ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

በተለይም በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የተከሰተው የፀጥታ መደፍረስ ሴቶችን ተጎጂ አድርጓል ያሉት ተሳታፊዎቹ ሰላምን ለማስፈን እና ዲሞክራሲን ለመገንባት ሴቶችን ማማከር ተገቢ መሆኑን ጠቁመዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.