Fana: At a Speed of Life!

የሀገር ውስጥ ባለሃብቶችን ተሳትፎ ማሳደግ የሚያስችሉ አሰራሮች እየተዘረጉ ነው

አዲስ አበባ፣ የካቲት 21፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የሀገር ውስጥ ባለሃብቶችን ተሳትፎ ማሳደግ የሚያስችሉ አዳዲስ አሰራሮችን እየዘረጋ መሆኑን የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ገለጸ።

የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽነር አቶ አበበ አበባየሁ የሃገር ውስጥ ባለሃብቶች ካለው ዓለም አቀፍ ልምድና እውቀት ማነስ ጋር በተያያዘ በተለይም በማምረቻው ዘርፍ ለመሰማራት ያላቸው ፍላጎት አነስተኛ መሆኑን ተናግረዋል።

በቅርቡ ተሻሽሎ የጸደቀው አዋጅ የሀገር ውስጥ ባለሃብቶችን ተሳትፎ ማሳደግ የሚያስችሉ በርካታ ማሻሻያዎች እንደተደረገበትም ገልፀዋል።

ከእነዚህ ውስጥ ከዚህ ቀደም ለሀገር ውስጥ ባለሃብቶች ዝግ የነበሩ ዘርፎች በሽርክና ከውጭ ባለሀብቶች ጋር በጋራ እንዲሰሩ የሚያደርግ አማራጮችን አስቀምጧል።

ከዚህ በተጨማሪም ኮሚሽኑ ባለፉት ስድስት ወራት ተሳትፎውን ለማሳደግ ሰፊ ትኩረት ሰጥቶ ሲሰራ መቆየቱን አስታውሰዋል።

በዚህም ወደ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ገብተው ስራ እንዲጀምሩ ከ17 ኩባንያዎች ጋር የመግባቢያ ስምምነት ተፈርሞ ሰባቱ ስራ መጀመራቸውን አስረድተዋል።

በትእግስት አብርሀም

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.