Fana: At a Speed of Life!

የሃረማያ እና መቐለ ዩኒቨርሲቲዎች 636 የህክምና ባለሙያዎችን አስመረቁ

አዲስ አበባ፣ ጥር 2፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የሃረማያ እና መቐለ ዩኒቨርሲቲዎች 636 የህክምና ባለሙያዎችን አስመረቁ።

የሃረማያ ዩኒቨርሲቲ 239 የህክምና ዶክተሮችን በዛሬው እለት አስመርቋል።

ዩኒቨርሲቲው በሃረማያ ዩኒቨርሲቲ የሃረር የህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች ነው ያስመረቀው።

በምረቃ ስነ ስርዓቱ ላይ የሃረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪን ጨምሮ የዩኒቨርሲቲው የቦርድ ሰብሳቢ ዶክተር ኢንጂነር ሃብታሙ ኢተፋና ሌሎች የክልልና የፌደራል የስራ ኃላፊዎች እንዲሁም የተመራቂ ቤተሰቦች ተገኝተዋል።

ከተመራቂዎቹ መካከል 56 የሚሆኑት ሴቶች መሆናቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

በሌላ በኩል መቐለ ዩኒቨርሲቱ በተለያዩ የህክምና መስኮች ያሰለጠናቸውን 397 ተማሪዎችን አስመርቋል።

ተመራቂዎቹ የህክምና ዶክተር፣ ሚድዋይፈሪ፣ ነርሲንግና ፋርማሲ የህክምና ዘርፎች የሰለጡ ናቸው።

በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የከተማ ልማትና ንግድ ኢንዱስትሪ ቢሮ ሃላፊ ዶክተር አብርሃም ተኸስተ በክብር እንግድነት ተገኝተዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.