Fana: At a Speed of Life!

የሃይማኖት ተቋማት ስለሰላም ፣አንድነት እና መቻቻል ከማስተማር ባለፈ በማህበረሰባዊ ልማት ላይ እያደረጉ ያለውን ተሳትፎ በይበልጥ ተቀራርበው ሊሰሩ ይገባል- ም/ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 13 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል እንዲመሰረት አስተዋጽዖ ላደረጉ አካላት የምስጋና መርሃ ግብር ተካሄደ።
በመርሃ ግብሩ ላይ የተገኙት ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ እንደገለጹት የሀይማኖት ተቋማት የእምነት ነጻነት ኖሯቸው እንዲደራጁ ከማድረግ ይልቅ እንዲከፋፈሉ ሲደረግ ቆይቷል ፡፡
በለውጡ ማግስትም መንግስት የእምነት ተቋማት የሚያቀርቡትን የመደራጀት እና የነፃነት ጥያቄ ለመመለስ ባደረገው ጥረት የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል እንዲመሰረት መደረጉን ጠቁመዋል፡፡
የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል ፕሬዚዳንት ዶክተር ኢያሱ ኤልያስ በበኩላቸው በኢትዮጵያ የወንጌል አማኞች ከ130 ዓመት በላይ እድሜ ያስቆጠሩ ቢሆንም እንደ እምነት ተቋም ሳይሆን እንደ ማህበር የሚታይ ነበር ብለዋል፡፡
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባደረገው 16ኛ መደበኛ ጉባኤ የኢትዮጵያ የወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል በይፋ ሙሉ ህጋዊ ሰውነት አግኝቶ በአዋጅ እንዲቋቋም መደረጉን የገለጹት ፕሬዚዳንቱ ለዚህም መንግስትን አመስግነዋል፡፡
በምስጋና መርሃ ግብሩ ላይ ከሁሉም ሀይማኖት ተቋማት የተውጣጡ የእምነት አባቶች፣የፌደራል እና የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ የመንግስት አመራሮች እና ተወካዮች መገኘታቸው ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፕሬስ ሴክሬቴሪያት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡-

https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.