Fana: At a Speed of Life!

የሃይማኖት አባቶች የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓልን በማስመልከት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 28 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የሃይማኖት አባቶች የ2013 ዓ∙ም የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓልን በማስመልከት ለምዕመናን የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ፓትርያርክ ብጹ አቡነ ማቲያስ፤ በነገው እለት የሚከበረውን የኢየሱስ ክርስቶስ ልደት በዓል አስመልክቶ የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት አስተላልፈዋል።

በዓሉ የታመሙትንና በማረሚያ ቤት ያሉትን በመጠየቅ፤ የተራቡን በመመገብ፣ የተጠሙትን በማጠጣትና የታረዙትን በማልበስ ለፈጣሪና ለወገናችን ያለንን ክብር የምናሳይበት ነው ብለዋል።

የክርስቶስ ልደት ሰማያውያንና ምድራውያን ስለ ክርስቶስ ክብርና ሰላም በሕብረት የዘመሩበት” በመሆኑ ሕዝበ ክርስቲያኑም በበጎ ስራ በጋራ በመሳተፍ በዓሉን ማክበር እንደሚገባ ነው የተናገሩት።

መላው ሕዝብ በጥበብና በማስተዋል እንዲንቀሳቀስ፣ ሁሉም ለሀገሩ፣ ለሃይማኖቱ፣ ለወገኑም ተገቢ ትኩረት በመስጠት በፀሎትና በሚችለው ሁሉ ትብብሩን አጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አሳስበዋል።

የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ሊቀጳጳሳት ብፁዕ ካርዲናል ብርሃነ እየሱስ በበኩላቸው “ሁሉም ኢትዮጵያዊ በዓሉን ሲያከብርም ሆነ ከዚያ በኋላ ያለ ልዩነት እርስ በርስ በመተጋጋዝና በመደጋጋፍ ለሀገር ሰላምና አንድነት በጋራ በመቆም ሊሆን ይገባል ብለዋል።

ህብረተሰቡ ወቅታዊ የጤና ስጋት ከሆነው ኮቪድ-19 ወረርሽኝ ራሱን እንዲጠብቅም ብፁዕ ካርዲናል ብርሃእነየሱስ ጥሪ አቅርበዋል።

በአዳነ በፍቃዱ

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.