Fana: At a Speed of Life!

የሃገር በቀል እሴቶች ለዘላቂ ሰላም ግንባታ፣ አብሮነትና ብሔራዊ መግባባት ትልቅ ትርጉም አላቸው – የሰላም ሚኒስቴር

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 19፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የሃገር በቀል እሴቶች ለዘላቂ ሰላም ግንባታ፣ አብሮነትና ብሔራዊ መግባባት ትልቅ ትርጉም እንዳላቸው የሰላም ሚኒስትሯ ወይዘሮ ሙፈሪሃት ካሚል ተናገሩ።

ከሁለት አመት በፊት በደረሰው  የአውሮፕላን አደጋ ሰብአዊነት ያሳዩ ሰዎች “የሰውነት ተምሳሌቶች” ናቸው በሚል ተመስግነዋል።

የምስጋና ፕሮግራሙን ሰላም ሚኒስቴር፣ ዕርቀ ሰላም ኮሚሽንና የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት አደጋው ደርሶበት በነበረው ስፍራ በመገኘት አከናውነዋል።

የሰላም ሚኒስትሯ ወይዘሮ ሙፈሪሃት ካሚል በስፍራው በመገኘት “የሰውነት ተምሳሌቶች” ለሆኑ ሁሉ  አመስግነዋል።

“የአካባቢው ነዋሪዎች የሰውነት መምህራን ናችሁ፤ የተጎጂ ቤተሰቦች መጽናኛ፣ ኢትዮጵያዊነትን በዓለም የሚያስተዋወቅ ዘመን ተሻጋሪ ተግባር ፈጽማችኋል” ብለዋል በመልእክታቸው።

“ለዚህ ሰብዓዊ ተግባራችሁ እናመሰግናችኋለን፤ ምስጋና ዕውቅና የመስጠት ስራውም የመስሪያ ቤቱ ብሔራዊ መግባባት መፍጠሪያ አንዱ አካል ነው” ብለዋል ሚኒስትሯ።

በንግግራቸው የሃገር በቀል እሴቶች ለዘላቂ ሰላም ግንባታ፣ አብሮነትና ብሔራዊ መግባባት ትልቅ ትርጉም ያላቸው መሆኑንም ገልጸዋል።

የኢትዮጵየ ዕርቀ ሰላም ኮሚሽን ሰብሳቢ ብፅዑ ካርዲናል አባ ብርሐነ ኢየሱስ ሱራፌል በበኩላቸው አሁን አሁን በኢትዮጵያ ሰብዓዊነት እየተሸረሸረ መምጣቱን እየተመለከትን ነው ብለዋል።

እንዲህ አይነት መልካም ዕሴቶችን ለመሸርሸር የሚሹ አካላት ቢያጋጥሙም በመልካም ምግባርና ስራቸው “የሰውነት ተምሳሌቶች” መኖራቸውን ጠቅሰዋል።

የተጎጂ ቤተሰብ ተወካዮችም 157 ተጎጂ ነፍሶችን በማክበርና በመዘከር ትልቅ ነገር ፈፅማችኋል፤ እናመሰግናለን ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.