Fana: At a Speed of Life!

የህብረተሰብ አቀፍ የአካል ብቃት ስፖርታዊ እንቅስቃሴው በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 18፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) ከተማ አቀፍ የሰላም ማህበረሰብ አቀፍ የአካል ብቃት ስፖርታዊ እንቅስቃሴ ተጀመረ።
“ለሀገሬ ሰላም ዘብ እቆማለሁ ለሀገር መከላከያ ሰራዊት ቅድሚያ እሰጣለሁ” በሚል መሪ ቃል የህብረተሰብ አቀፍ የአካል ብቃት ስፖርታዊ እንቅስቃሴው በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ተካሄደ ።
በአዲስ አበባ ስፖርት ኮሚሽን አዘጋጅነት በቅርቡ በተዋቀረው አዲሱ ለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ የካ አባዶ የጋራ መኖሪያ ቤት የማህበረሰብ አቀፍ የአካል ብቃት ስፖርታዊ እንቅስቃሴ ተደርጓል ።
በአካል ብቃት ስፖርታዊ እንቅስቃሴው ላይ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የመንግስት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት አስተባባሪው አቶ ጃንጥራር አባይን ጨምሮ የፌዴራል ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር ኤልያስ ሽኩር ፣የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ፕሬዚዳንት ዶክተር አሸብር ወልደጊዮርጊስ ፣ የአዲስ አበባ ከተማ ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር በላይ በላይ የለሚ ኩራ ፣ የቦሌ ፣ የየካ ክ/ከ ዋና ስራ አስፈፃሚዎች እና ከሶስት ሺህ በላይ የየካ አባዶ የጋራ መኖሪያ ቤት ነዋሪዎች ተሳታፊ ሆነዋል ።
የአካል ብቃት እንቅስቃሴው በየጊዜው በቀጣይነት የሚካሄድ ነው።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.