Fana: At a Speed of Life!

የህብረቱ የመሪዎች ጉባኤ በአዲስ አበባ መካሄድ ኢትዮጵያ ሠላም አይደለችም የሚለውን የጠላት ሃሳብ ከመሰረቱ ነቅሎ የሚጥል ነው – አምባሳደር ዲና ሙፍቲ

አዲስ አበባ፣ ጥር 12፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በቀጣይ ሣምንት በአዲስ አበባ የሚካሄደው የአፍሪካ ኅብረት 35ኛ የመሪዎች ጉባኤ ኢትዮጵያ ሠላም አይደለችም የሚለውን የጠላት ሃሳብ ከመሰረቱ ነቅሎ የሚጥል መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ገለጹ፡፡
ጉባኤውን ከማስቀረት ባለፈም የአፍሪካ ኅብረት መቀመጫን ከኢትዮጵያ ለማንሳት ዘርፈ ብዙ ጥረቶች ሲደረጉ መቆየታቸውን ያነሱት ቃል አቀባዩ ፥ ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ያላትን ሚና ከግምት በማስገባት በተሠራ ሰፊ የዲፕሎማሲ ሥራ ጉባዔው አዲስ አበባ እንዲካሄድ ተወስኗል ብለዋል።
አፍሪካውያን ተጽእኖ ፈጣሪዎች እና ታዋቂ ሰዎችም በዲፕሎማሲው ሥራ የራሳቸው አበርክቶ ነበራቸውም ብለዋል ቃል አቀባዩ።
የጉባኤው ዋና አጀንዳ አልሚ ምግብ ላይ መሆኑን የገለጹት ቃል አቀባዩ፥ ጉባኤው የተሳካ እንዲሆን ግብረ-ኃይል ተቋቁሞ ሰፊ ዝግጅት እየተደረገ ነው ብለዋል።
በመግለጫው ዜጋ ተኮር ዲፕሎማሲን በሚመለከት የዳያስፖራ ማኅበረሰብ አባላት በኢንቨስትመንት፣ በመልሶ ግንባታ፣ ጉዳት የደረሰባቸው አካባቢዎችን እና የቱሪዝም መዳረሻዎችን በመጎብኘት፣ በሲምፖዚየም እና በአጠቃላይ በሀገራዊ ጉዳዮች ሰፊ እንቅስቃሴ እያደረጉ ነው ብለዋል።
አሁንም የዳያስፖራ ማህበረሰብ አባላት ወደ ኢትዮጵያ እየገቡ መሆኑን አምባሳደር ዲና ተናግረዋል።
በዙፋን ካሳሁን እና ቆንጅት ዘውዴ
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.