Fana: At a Speed of Life!

የህክምና መገልገያ መሳሪያዎች እና የመድሃኒት አቅርቦት ችግርን በዘላቂነት ለመፍታት አሰራሩን ማሻሻል ይገባል – ዶክተር ሊያ ታደሰ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 14 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በሃገር አቀፍ ደረጀ ወጥ ያልሆነውን የህክምና መገልገያ መሳሪያዎች እና የመድሃኒት አቅርቦት ችግር በዘላቂነት ለመፍታት አሰራሩን ማሻሻል እንደሚገባ የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ ተናገሩ፡፡

የጤና ሚኒስቴር የ6 ወር የስራ እቅድ አፈጻጸም በፍላግሺፕ ኢኒሼቲቭ እና በዋና ዋና ተግባራት አፈፃፀም ላይ ትኩረት አድርጎ እየገመገመ ነው፡፡

በመድረኩ ላይም ሚኒስትሯ የእቅድ ወጥነት፣ መናበብና ቅንጅታዊ አሰራሮችን ዳይሬክቶሬቶች ከውስጥም ሆነ ከውጭ ካሉ ተቋማት ጋር ትስስሩን ማጠናከር ይገባቸዋል ብለዋል፡፡

የተጀመሩ ስራዎች በቀጣይ 6 ወራት መጠናቀቅ እንዳለባቸውና ሌሎች ያልተያዙ ዋና ዋና ስራዎች በዕቅድ ክለሳ እንዲካተቱ አቅጣጫ የተቀመጠ ሲሆን በቀጣይም ስራዎችን ወቅታዊ ሁኔታዎችን ባገናዘበ መልኩ መስራት ይገባልም ነው ያሉት፡፡

የጤና አገልግሎት ጥራትና ደህንነት፣ የህሙማን ደህንነት፣ የጤና ስርአት አመራርና አስተዳደር እንዲሁም የሪፈራል አሰራሩን ማሻሻልና ኮቪድ 19ኝን ጨምሮ ተላላፊና ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎችን መከላከልና መቆጣጠር በቀጣይ ስድስት ወራት በትኩረት የሚሰራባቸው ናቸው ተብሏል፡፡

ባለፉት 6 ወራት በአንዳንድ አከባቢዎች የሚስተዋሉ የጸጥታ መደፍረስ ችግሮች የእቅድ አፈጻጸም ላይ ችግር ማስከተላቸው ተጠቁሟል፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.