Fana: At a Speed of Life!

የህወሃት የሽብር ቡድን ዳግም የጦር ነጋሪት መጎሰም መጀመሩ ቡድኑ ያለጦርነት መኖር እንደማይችል ያሳያል-ምሁራን

አዲስ አበባ ፣ግንቦት 4 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የህወሃት የሽብር ቡድን ዳግም የጦር ነጋሪትን መጎሰም መጀመሩ ቡድኑ ያለጦርነት መኖር እንደማይችል ያሳያል ሲሉ ምሁራን ተናገሩ፡፡

አሸባሪ ቡድኑ በአፈቀላጤዎች በኩል በትግራይ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች እየዞረ የጦርነት ቅስቀሳና ዝግጅት እያደረገ መሆኑን የሚያመላክቱ መረጃዎች እየወጡ ነው፡፡

በእነዚህ የቅስቀሳ መድረኮች ህዝቡን አስገድዶ የማዝመት፣ የስንቅ መዋጮ ግዳጅና ያለእድሜ ገደብ ዝመቱ የሚሉ ጫናዎች ከሽብር ቡድኑ እየቀረበ ነው፡፡

በየአካባቢው በተደረጉ መድረኮችም የሽብር ቡድኑ ከፍተኛ ባለስልጣናት ሲዝቱ ተስተውሏል፡፡

በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ምሁሩ ሱራፌል ጌታሁን፥ የሽብር ቡድኑ ያለጦርነት መኖር ስለማይችል ዳግም የጥፋት መንገድን መምረጡን ያነሳሉ፡፡

የትግራይ ህዝብ ሰላምና መረጋጋት ጥፋቱን ስለሚያጋልጥበት ሁልጊዜ ጠላት እየፈጠረ ማህበራዊ እረፍት እንደሚነሳውም ተናግረዋል፡፡

በጎንደር ዩኒቨርስቲ የህግ መምህርና ተመራማሪው አዳነ ማንዴ በበኩላቸው፥ ቡድኑ ዳግም ወደ ጦርነት የመግባት ፍላጎት ያደረበት ያልሰመረለትን ኢትዮጵያን የማፍረስ ቅዠቱን እውን ለማድረግ ነው ብለዋል፡፡

ከጥፋት መንገዱ ለማስቆምም በተለይም የትግራይ ልሂቃንና ህዝብ በቃህ ሊሉት ይገባል ሲሉ ምሁራኑ ተናግረዋል፡፡

የኢትዮጵያ ህዝብ በጋራ በመቆምና ለከፋፋይ አጀንዳዎች ባለመጭበርበር ሀገሩን ሊጠብቅ ይገባልም ብለዋል ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር ቆይታ ያደረጉት ምሁራን፡፡

በአፈወርቅ እያዩ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.