Fana: At a Speed of Life!

የህወሃት ጁንታ በሚያናፍሰው ፕሮፓጋንዳ ህዝቡ መደናገር እንደሌለበት የሰራዊቱ አባላት አመለከቱ

አዲስ አበባ ፣ህዳር 15 ፣2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የህወሃት ጁንታ በሚያናፍሰው ፕሮፓጋንዳ ህዝቡ ሊደናገር እንደማይገባው በህግ ማስከበር ዘመቻ ላይ የተሰማሩ የአገር መከላከያ ሰራዊት አባላት ተናገሩ።
ጁንታውን በመቆጣጠር ለህግ ለማቅረብ ዝግጁ መሆናቸውንም አረጋግጠዋል።
ኢዜአ ያነጋገራቸው የሰራዊቱ አባላት እንደገለጹት፤ የህወሃት ጁንታ የሃሰት ፕሮፓጋንዳ የተለመደና ሁሉም የሚያውቀው ነው።
‘ጁንታው አጥፍቶ አላየሁም፣ ሰርቆ ደብቆ አልነበርኩም’ በማለት እንዲሁም የሌለ ነገር ፈጥሮ መዋሸት የተካነበት ስራው መሆኑን ገልጸዋል።
“በመሆኑም ህዝቡ በህወሃት የፈጠራ ወሬ ሊደናገርና ሊሸበር አይገባውም” ብለዋል የሰራዊቱ አባላት።
በህወሃት ጁንታ ታፍኖ የኖረውና ነፃነት የሚሻው የትግራይ ህዝብ የሰራዊቱን ድጋፍ በመፈለጉ ህግ የማስከበር ዘመቻው በውጤታማነት መቀጠሉን ገልጸው፤ “ለአገራችን ልእልና መከበር ዝግጁ ነን ሰራዊቱ እስካለ ድረስ ህዝቡም ስጋት አይግባው” ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
“የአገር መከላከያ ሰራዊት የጁንታውን እጅ ይዞ ለህግ ያስረክባል እንጂ ለማንም ጠላት እጅ የሚሰጥ አይደለም” ያሉት የሰራዊቱ አባላት፤ ይህንን የህወሃት ጁንታ ጠንቅቆ እንደሚያውቀውም ገልጸዋል።
“በህግ ማስከበር ዘመቻው የትግራይ ህዘብ በየደረስንበት ሁሉ ያሳየን ፍቅርና አክብሮትም ለበለጠ ግዳጅ አነሳስቶናል” ብለዋል።
የህወሃት ጁንታ ህዝቡን በተለያዩ የውሸት ፕሮፓጋንዳዎች ሲያደናግር ቢቆይም ሰራዊቱ በተቆጣጠረባቸው አካባቢዎች በርካቶች እውነታውን እንደተረዱም መግለጻቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.