Fana: At a Speed of Life!

የህወሓት ቡድን የፈፀመው ተግባር አሰቃቂ፣ ጭካኔ የተሞላበትና በዓለም አቀፍ ወንጀል የሚያስጠይቅ ነው- የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አፈጻጸም መርማሪ ቦርድ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 1፣ 2013 (ኤፍቢሲ) ቦርዱ በባህርዳር ፣ጎንደር ፣ዳንሻ ፣ሁመራና ማይካድራ በመገኘት በጽንፈኛው የህወሓት ቡድን የተፈጸመውን ጥቃትና ያደረሰውን ውድመት እንዲሁም አሁን ያለበትን አጠቃላይ ሁኔታ ተመልክቶ የደረሰበትን ሪፖርት ይፋ አድርጓል።

በዚህ ጥቃት ከ700 በላይ የሚሆኑ ንፁሃን ዜጎች የሕወሓት ጁንታ ባደራጀው ‘ሳምሪ’ በተባለ ኢ-መደበኛ ቡድን እና ሌሎች አካላት በጅምላ መጨፍጨፋቸውን አስታውቋል።

በሪፖርቱም የህወሓት ጽንፈኛ ቡድን የፈጸመው አሰቃቂ፣ ጭካኔ የተሞላበትና ኢ-ሰብዓዊ ድርጊት በሀገር ቤት ብቻ ሳይሆን በዓለም አቀፍ ህግም በወንጀል የሚያስጠይቀው መሆኑን አስታውቋል።
ጽንፈኛ ቡድን በፈጸመው ጥቃት ምክንያት የተፈናቀሉ ዜጎች በጎንደር አካባቢ ተጠልለው እንደሚገኙና አስፈላጊው ድጋፍ እየተደረገላቸው እንደሚገኝም ቦርዱ ዛሬ ይፋ ባደረገው ሪፖርት አስታውቋል።
አያይዞም ጉዳት የደረሰባቸው ዜጎች ህክምናና ክትትል እየተደረገላቸው መሆኑን አመላክቷል።
ቦርዱ አሁን አካባቢዎቹ ላይ አንጻራዊ መረጋጋት በመኖሩ አስፈላጊ የሚባሉ መሰረታዊ ነገሮች እንዲሟሉና በቀጣይም ትኩረት ቢሰጥባቸው ያላቸውን ምክረ ሀሳቦች ለሚመለከታቸው አካላት ማስታወቁን ገልጿል።
በዚህም የተፈናቀሉ ወገኖችን መልሶ ማቋቋምና ሰብአዊ ድጋፎችም ተጠናክረው እንዲቀጥሉ መርማሪ ቦርዱ በሪፖርቱ ማመላከቱን ነው የገጸው።
በሀይለየሱስ ስዩም
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል
https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.