Fana: At a Speed of Life!

የህወሓት ጁንታ ከማረሚያ ቤት በመልቀቅ ለዘረፋ ያሰማራቸውን ወንጀለኞች በቁጥጥር ስር የማዋሉ ተግባር ተጠናክሮ ቀጥሏል

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 11 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የህወሓት ጁንታ ከማረሚያ ቤት በመልቀቅ ለዘረፋ ያሰማራቸውን ወንጀለኞች በቁጥጥር ስር የማዋሉ ተግባር ተጠናክሮ መቀጠሉን የፌደራል ፖሊስ አስታወቀ።

በፌደራል ፖሊስ የወንጀል መከላከል ዘርፍ ሃላፊ ምክትል ኮሚሽነር መላኩ ፋንታ ዛሬ በመቀሌ ከተማ ለመገናኛ ብዙሃን መግለጫ ሰጥተዋል።

ምክትል ኮሚሽነር በዚህን ወቅት ጁንታው ከተሞችን ለቆ ከመሸሹ በፊት በማረሚያ ቤት የነበሩ ወንጀለኞችን መሳሪያ አስታጥቆ በመልቀቅ በከተሞች አካባቢ ዝርፊያ እንዲፈጽሙ ማድረጉን ነው የገለጹት።

እነዚህ ወንጀሎች የመንግስት ተቋማትን ንብረት ጭምር መዝረፋቸውን መናገራቸውን ኢዜአ ዘግቧል

የፌደራል ፖሊስ ከህብረተሰቡ ጋር በመቀናጀት ወንጀለኞቹን በቁጥጥር ስር የማዋሉን ስራ አጠናክሮ መቀጠሉንም አስታውቀዋል።

ወንጀለኞቹ የታጠቁትን የጦር መሳሪያዎች የማስፈታቱ ተግባር እየተከናወነ መሆኑንም ተናግረዋል።

በተጨማሪም ህገ-ወጡ የህወሃት ጁንታ በመንግስት ተቋማት ያሉ ሰነዶችንና ሰነድ የያዙ ኮምፒውተሮችን አቃጥሎ መሸሸኑም ገልጸዋል።

ይህም ቡድኑ ከራሱ ስልጣን ውጭ ለህዝብ ምንም አይነት ዴንታ የሌለው መሆኑን ያመላክታል ብለዋል።

የአካባቢው ማህበረሰብ የፌደራል ፖሊስ እያከናወነ ያለውን ተግባር በመደገፍ ረገድ ጉልህ ሚና እያበረከተ መሆኑንም ምክትል ኮሚሽነሩ ተናግረዋል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.