Fana: At a Speed of Life!

የህዝብ ለህዝብ ግንኙነትን ማጠናከር የሚያስችሉ ስራዎች በሀገር አቀፍ ደረጃ ይሰራሉ – የሰላም ሚኒስቴር

አዲስ አበባ፣ የካቲት 18፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የህዝብ ለህዝብ ግንኙነትን ማጠናከር የሚያስችሉ ስራዎች በሀገር አቀፍ ደረጃ እንደሚሰሩ የሰላም ሚኒስቴር አስታወቀ።

ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር ቆይታ ያደረጉት በሚኒስቴሩ የሰላም ግንባታ ዳይሬክተር አቶ ወንድወሰን መኮንን፥ በሃገር አቀፍ ደረጃ የህዝብ ለህዝብ ግንኙነትን ለማጠናከር የተሰሩ ስራዎች ውጤት ማምጣታቸውን አንስተዋል።

ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ መሰል ስራዎችን አጠናክሮ ለመስራት ማቀዱን ጠቁመው፥ በተለይም የምክክር መድረኮች እና ህዝባዊ ኮንፈረንሶችን ማዘጋጀት ዋነኞቹ ተግባራት ናቸው ብለዋል።

ከዚህ ባለፈም ችግር በሚታይባቸው አካባቢዎች የእርቅ እና የሽምግልና ስርአቶችን በመጠቀም ዘላቂ ሰላምን የመፍጠር ስራዎች እስከታች ድረስ ባለው መዋቅር እንደሚሰሩም ጠቅሰዋል።

አያይዘውም እንደ ሀገር የሚታዩ ችግሮችን እና አለመግባባቶችን ለመፍታት በተለይም ምሁራን ሚናቸውን እንዲወጡ የማድረግ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑንም ጠቁመዋል።

ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር ቆይታ ያደረጉ ምሁራን በበኩላቸው፥ ሁሉም ዜጋ ሰላምን የጋራ ሀብት በማድረግ ሀገራዊ አንድነትን መፍጠር ይገባዋል ነው ያሉት።

በክልሎች መካከል የሚታዩ አለመግባባቶችን ለመፍታት እና የህዝቡን ግንኙነት ለማጠናከርም ሁሉም ዜጋ ሰላምን ቀዳሚ በማድረግ መስራት እንደሚጠበቅበትም አጽንኦት ሰጥተዋል።

ምሁራኑ አክለውም ሰላምን የጋራ ሀብት በማድረግ መስራት ከሀገርም አልፎ በዓለም ተደማጭ ለመሆን ያበቃል ሲሉ አስረድተዋል።

በዙፋን ካሳሁን

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.