Fana: At a Speed of Life!

የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት እና ተጠሪ ተቋማት በሃረሪ ክልል አረንጓዴ አሻራቸውን አሳረፉ

አዲስ አበባ ፣ሐምሌ 27፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢፌዲሪ የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት እና ለምክር ቤቱ ተጠሪ የሆኑ ተቋማት በሃረሪ ክልል የችግኝ ተከላ እና ለአቅመ ደካሞች የመኖሪያ ቤት እድሳት አደረጉ፡፡
 
የምክር ቤቱ አባላት እና ተጠሪ ተቋማቱ የሃረሪ ክልል ከፍተኛ የሥራ ሃላፊዎች በተገኙበት ነው በሃማሪሳ የባህል ማዕከል የችግኝ ተከላ በማድረግ አረንጓዴ አሻራቸውን ያሳረፉት፡፡
 
አመራሮቹ ከዚህ በተጨማሪም በክልሉ ሃኪም ወረዳ በመገኘት አቅመ ደካማ የሆኑ ግለሰብ የመኖሪያ ቤት ሙሉ ወጪውን በመቻል እድሳት አድርገዋል፡፡
 
የመኖሪያ ቤት እድሳት የተደረገላቸው ወይዘሮ የትናየት ዘለቀ ለ2ዐ ዓመታት ምቹ ባልሆነ ቤት ከ5 የቤተሰቡ አባላት ጋር በከፍተኛ ችግር ይኖሩ እንደነበር ገልጸዋል፡፡
 
ወይዘሮ የትናየት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እና ተጠሪ ተቋማቱ ባደረጉት የበጐ ሥራ መደሰታቸውን ተናግረዋል፡፡
 
በምክር ቤቱና በተጠሪ ተቋማቱ በተጀመረው የበጐ ፈቃድ አገልግሎት በሃረሪ ክልል የተለያዩ ወረዳዎች የ14 የአቅመ ዳካማ መኖሪያ ቤቶች እድሳት እንደሚደረግላቸው ከምክርቤቱ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
 
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
 
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
 
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
 
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
 
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
 
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
 
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.