Fana: At a Speed of Life!

የህዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም ለሶስት ተቋማት እውቅና ሰጠ

አዲስ አበባ፣ ጥር 13፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ህዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም በመረጃ ተደራሽነት መልካም አፈፃፀም ላሳዩ ሶስት ተቋማት እውቅና ሰጥቷል።

ተቋሙ እውቅና የሰጠው ለጤና ሚኒስቴር፣ ለኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩትና ለተባበሩት መንግስታት ድርጅት የዓለም አቀፍ ልማት ፕሮግራም (ዩ.ኤን.ዲፒ) ነው።

ዕውቅናውን የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምክትል አፈጉባኤ ወይዘሮ ሽታዬ ምናለ ለተቋማቱ የስራ ሀላፊዎች አበርክተዋል።

ተቋማቱ እውቅና የተሰጣቸው በኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ ከተከሰተ ጀምሮ የበሽታውን ስርጭት ለመግታት መረጃዎችን ወደ ህዝብ በማድረስ ረገድ ባበረከቱት አስተዋጽኦ መሆኑን የኢትዮጵያ የህዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም ዋና ጠባቂ ዶክተር እንዳለ ሀይሌ ተናግረዋል።

እውቅናው ሌሎች ተቋማት መረጃ በማድረስ ረገድ ሃላፊነታቸውን በአግባቡ እንዲወጡ ተነሳሽነት እንደሚፈጥርም ጨምረው ገልጸዋል።

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምክትል አፈጉባኤ ወይዘሮ ሽታዬ ምናለ በበኩላቸው ሁሉም ተቋማት ትክክለኛና ተጨባጭ መረጃ ለህብረተሰቡ ማድረስ ሃላፊነታቸውን በአግባቡ መወጣት እንዳለባቸው ማሳሰባቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.