Fana: At a Speed of Life!

የህዳሴው ግድብ የውሃ ሙሌት የግድቡን ተፈጥሯዊ የግንባታ ሂደት በጠበቀ መልኩ እየተከናወነ ነው – ዶ/ር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 8፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የህዳሴው ግድብ የውሃ ሙሌት የግድቡን ተፈጥሯዊ የግንባታ ሂደት በጠበቀ መልኩ እየተከናወነ መሆኑን የውሃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ዶክተር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ ተናገሩ።

ሚኒስትሩ በህዳሴው ግድብ ዙሪያ ኢትዮጵያ፣ ሱዳን እና ግብጽን ጨምሮ ሌሎች የአፍሪካ ሃገራት የተሳተፉበት ውይይት መካሄዱን ዛሬ በሰጡት መግለጫ ተናግረዋል።

በውይይቱ ላይ በተወሰኑ ነጥቦች ላይ መግባባት ላይ መደረሱንም አስረድተዋል።

ከዚህ ባለፈ ግን በአንዳንድ ጉዳዮች ላይ በኢትዮጵያ ዘላቂ ጥቅም ላይ ተፅዕኖ የሚኖራቸው ነጥቦች ላይ ጥንቃቄ ማድረግ በማስፈለጉ ልዩነት እንደነበርም አንስተዋል።

የግድቡ አሞላልም የግድቡን ተፈጥሯዊ የግንባታ ሂደት በጠበቀ መልኩ እየተከናወነ ነው ብለዋል።

ከዚህ ጋር ተያይዞም አሁን ላይ ግድቡን በተመለከተ በሳተላይት የሚታዩ ምስሎች ትክክለኛ መሆናቸውንም ገልጸዋል።

በውይይቱ ላይ ሶስቱን ሃገራት ጨምሮ ከኬንያ፣ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ፣ ማሊ፣ ማዳጋስካር እና ደቡብ አፍሪካ የተውጣጡ 11 ባለሙያዎች ተሳትፈዋልም ነው ያሉት።

በለይኩን ዓለም

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.