Fana: At a Speed of Life!

የህዳሴ ግድብ በሱዳን ሲፈጠር የነበረን ጎርፍ በማስቀረት ተጨማሪ የእርሻ ቦታ እንደሚያስገኝላቸው የሱዳን አርሶ አደሮች ተናገሩ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 13፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ በሱዳን ሲፈጠር የነበረን የጎርፍ አደጋ በማስቀረት ተጨማሪ የእርሻ ቦታ እንዲያገኙ አድል እንደሚፈጥርላቸው የሱዳን አርሶ አደሮች ተናገሩ።

አልጀዚራ ያነጋገራቸው እነዚህ የሱዳን አርሶ አደሮች ግድቡ በግብፅ “ግሬት ዳም” አካባቢ የተስተካከለ የውሃ ፍሰት በመፍጠር ተጨማሪ የእርሻ ስፍራን እንደሚያጎናፅፋቸው ነው ከወዲሁ የተናገሩት።

የግብፅ “ግሬት ዳም” በሰሜናዊ ሱዳን ድንበር ላይ የሚገኝ ግድብ ነው።

የህዳሴ ግድብ መገንባት በየዓመቱ ጎርፍ በምርታቸው ላይ ያደርስ የነበረውን ጉዳት እንደሚቀንስ በመጠቆምም በግድቡ ላይ ያላቸውን ተስፋ ለአልጀዚራ ተናግረዋል።

በቀጣይ የወንዙ የውሃ ፍሰት የተስተካከለ እንደሚሆን በመግለፅም ከዚህ ቀደም በዓመት ሁለት ጊዜ ብቻ ያርሱ የነበረውን መሬት ሶስት ጊዜ ወደማረስ እንደሚሸጋገሩ ነው የጠቆሙት።

የሱዳን የውሃና መስኖ ሚኒስትሩ ያስር አባስ በበኩላቸው ኢትዮጵያ የህዳሴ ግደብ የውሃ ሙሌትን በያዝነው ወር ብትጀምር ሱዳን ተጠቃሚ እንደምትሆንም ነው ለአልጀዚራ አረብኛ የተናገሩት።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.