Fana: At a Speed of Life!

የህዳሴ ግድብ ግንባታ የአባይን የውሃ ተፈጥሯዊ ፍሰት አይቀይርም – አምባሳደር አለማየሁ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 20፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የህዳሴ ግድብ ግንባታ የአባይን የውሃ ተፈጥሯዊ ፍሰት እንደማይቀይርና ግንባታው እንደማይቆም በሩሲያ የኢትዮጵያ አምባሳደር አለማየሁ ተገኑ ገለጹ።
አምባሳደር አለማየሁ ተገኑ በየዕለቱ ከሚታተው ኮምሶሞለስካያ ፕራቫድ ጋዜጣ ጋር ቆይታ አድርገዋል።
አምባሳደሩ በቆይታቸው ከህዳሴ ግድብ ጋር በተያያዘ በተለይ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የሰጡትን አስተያየት የተመለከቱ ጉዳዮችን አንስተዋል።
የአባይ ወንዝ ከሀይል ማመንጫ ግንባታው ጋር በተያያዘ ተፈጥሯዊ ፍሰቱን አይቀይርምም ነው ያሉት።
ኢትዮጵያ በዋሽንግተን በምንም አይነት ጉዳይ ስምምነት ላይ አልደረሰችም ያሉት አምባሳደሩ የውይይቱ አካል ባልሆነ ነጥብ ላይ እንድትፈርም ጥሪ ቀርቦላት
እንደነበርም አስታውሰዋል።
ኢትዮጵያ ህጋዊ ፍላጎቷን እንድታጣ የሚያደርጋትን ፍትሃዊ ያልሆነ የስምምነት ጥረት እንደማትቀበልም ጠቅሰዋል፡፡
አምባሳደሩ የኢትዮጵያ እና ሩሲያን የሁለትዮሽ ግንኙነትን በተመለከተ እና በሌሎች ጉዳዮች ላይ ለጋዜጣው ሀሳባቸውን አጋርተዋል።
በተመሳሳይ 15 ለሚሆኑ የሩሲያ መገናኛ ብዘሃን በሰጡት መግለጫ ከህዳሴው ግድብ ጋር በተያያዘ ካነሷቸው ሀሳቦች በተጨማሪ በኢትዮጵያ ውስጥ እየተካሄደ
ስላለው ለውጥ አንስተዋል።
እንዲሁም ስለ ኢትዮጵያ የምስራቅ አፍሪካ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ፣ ከሩሲያ ጋር ስላላት ግንኙነት፣ የኢኮኖሚ አቅሞች፣ የኢንቨስትመንት አማራጮች እና የቱሪዝም መስህቦች ለጋዜጠኞቹ ማብራሪያ ሰጥተዋል።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.