Fana: At a Speed of Life!

የላቀ አፈፃፀም ላስመዘገቡ የገቢዎች ሚኒስቴር እና ተጠሪ ተቋማት ሰራተኞች እውቅና እና ሽልማት ተበረከተ

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 14 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የላቀ አፈጻጸም ላስመዘገቡ የገቢዎች ሚኒስቴር እና ተጠሪ ተቋማት እውቅና እና ሽልማት ተበረከተ፡፡

የእውቅና እና ሽልማት ስነ ስርአቱ ባለፈው በጀት አመት 233 ነጥብ 7 ቢሊየን ብር ገቢ እንዲገኝ ላስቻሉ አመራሮችና ሰራተኞች ነው የተሰጠው፡፡

የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንንም እውቅና እና ሽልማቱን ለሰራተኞቹ እና አመራሮች አስረክበዋል፡፡

የገቢዎች ሚኒስትር ላቀ አያሌው ለሚፈለገው ሃገራዊ ሁለንተናዊ ለውጥ እና ልማት የሚኒስቴሩ ሰራተኞች ሚና ወሳኝ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በዛሬው እለት ለሰራተኞቹ የተሰጠው እውቅና እና ሽልማትም ሰራተኞቹ የሚያሳዩት አፈጻጸም በተያዘው በጀት ዓመት ተጠናክሮ እንዲቀጥል ያግዛልም ብለዋል፡፡

ሚኒስቴሩ በዘንድሮው ሩብ ዓመት 63 ነጥብ 3 ቢሊየን ብር መሰብሰቡ ተገልጿል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.