Fana: At a Speed of Life!

የሌተናል ኮለኔል ፍስሐ ደስታ የቀብር ሥነ ስርዓት ተፈጸመ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 30፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ሕዝባዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የቀድሞው ምክትል ፕሬዚዳንት ሌተናል ኮለኔል ፍስሐ ደስታ የቀብር ሥነ ስርዓት በቅድስት ስላሴ ካቴድራል ተፈጸመ።
በቀብር ስነ ስርዓቱ ላይ ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋኅዶ ቤተክርስቲያን ፓትርያርክን ጨምሮ የሃይማኖት አባቶች እንዲሁም የቀድሞ የስራ ባልደረቦች እና ወዳጅ ዘመዶቻቸው ተገኝተዋል፡፡
ዓድዋ ውስጥ የተወለዱት ሌተናል ኮሎኔል ፍሰሐ÷ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርታቸውን በዓድዋ ንግሥተ ሳባ፣ ሁለተኛ ደረጃን ትምህርታቸውን ደግሞ አዲግራት ውስጥ በሚገኘው አግአዚ ትምህርት ቤት ተከታትለዋል።
የቀድሞው የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ሐረር ጦር አካዳሚ 3ኛ ኮርስ ምሩቅ መኮንን የነበሩት ሌተናል ኮሎኔሉ፥ በደርግ ዘመን በተለያዩ የኃላፊነት ቦታዎች ላይ አገልግለዋል።
ከደርግ ውድቀት እና ኢሕአዴግ አዲስ አበባን ከተቆጣጠረ በኋላ ለ20 ዓመታት ያህል በእስር የቆዩ ሲሆን፥ ከእስር ከወጡ በኋላም በደርግ ዘመን ስላለፉባቸው ሁኔታዎች የሚተርክ “አብዮቱ እና ትዝታዬ” የሚል መጽሐፍ ፅፈዋል።
ሌተናል ኮሎኔል ፍስሐ ባለትዳርና የአንድ ልጅ አባት ነበሩ፡፡
በሃይማኖት ኢያሱ
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.