Fana: At a Speed of Life!

የሐረማያ ዩኒቨርስቲ የዘንድሮ ተመራቂ ተማሪዎች ከሁለት ሚሊዮን ብር በላይ በሚገመት ያከናወኑዋቸው ፕሮጀክቶች ተመረቁ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 7፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የሐረማያ ዩኒቨርስቲ የህክምናና ጤና ሳይንስ የዘንድሮ ተመራቂ ተማሪዎች በሀረሪ ክልል ከሁለት ሚሊዮን ብር በላይ በሚገመት ያከናወኖቸው ፕሮጀክቶች ተመረቁ።

“ለማህበረሰባች ለመክፈል ዝግጁ ነን” በሚል መርሃግብር 355 የጤና ተመራቂ ተማሪዎች በሃረሪ ክልል በከተማና በገጠር በተመረጡ ዘጠኝ አካባቢዎች ላይ ፕሮጀክቶቹን ያከናወኑት።

ሀረር በሚገኘው የሐረማያ ዩኒቨርስቲ የህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ በተለያዩ የሙያ መስኮች ትምህርታቸውን ተከታትለው ሲያጠናቅቁ ከመመረቃቸው በፊት ወደ ማህበረሰቡ በመሰማራት የመስክ የቡድን ስልጠና ይከናውናሉ፤በዚህም የህብረተሰቡን ችግሮች የሚቀርፉ የተለያዩ ፕሮጀክቶችን ይሰራሉ።

የዘንድሮ ተመራቂ ተማሪዎችም ሃብት በማፈላለግ ከሁለት ሚሊዮን ብር በሚበልጥ ወጪ በዘጠኝ ሳይቶች ላይ የመፀዳጃ ቤቶችን ግንባታ፣ በእጅ በፓምፕ የሚሰራ ውሃ፣ በተለያዩ ትምህርት ቤቶችና ህዝብ በሚበዛባቸው አካባቢዎች የእጅ መታጠሚያዎችን ገንብተው ለህብረተሰቡ አስረክበዋል።

ተመራቂ ተማሪዎቹ በደም ልገሣ፣ በአካባቢ ፅዳትና ስለ ኮቪድ 19 አስከፊነትና መከላከያ መንገዶች ለህብረተሰቡ ግንዛቤን አስጨብጠዋል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም ለ45 የጎዳና ተዳዳሪዎችና ስራ አጥ የሆኑ ሴቶች ስራ መጀመር እንዲችሉ የጫማ መጥረጊያ ቁሳቁሶችንና ለርቢ የሚሆኑ የዶሮ ዝርያዎችን በመስጠት ስራ እንዲጀምሩ አድርገዋል።

የሀረር ጤናና ህክምና ሳይንስ ኮሌጅ ዋና ስራ አስፈጻሚ ዳይሬተር ዶክተር ያደታ ደሴ ተመራቂ ተማሪዎች በተመደቡበት የተግባር ተኮር ስልጠና ሳይቶች የህብረተሰብን የጤና ችግር የሚቀርፉና ፍላጎቱን መሰረት ያደረጉ ፕሮጀክቶችን ማህበረሰቡን ባሳተፈ መልኩ ችግር ፈቺ ፕሮጀክቶችን በመቅረጽ ለማህበረሰብ የጤና አገልግሎት መስጠታቸውን ገልጸዋል።

ፕሮጀክቶቹ በተሰሩባቸው አካባቢዎች የሚኖሩ የህብረተሰብ ክፍሎች የተሰሩት ስራዎች ችግሮቻቸውን የሚቀርፉላቸው መሆኑን አመልክተዋል።

ፕሮጀክቶቹን የተለያዩ የስራ ኃላፊዎች መርቀው ለአገልግሎት እንዲውሉ አድርገዋል።

በተሾመ ኃይሉ

 

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት መተግበሪያን https://play.google.com/store/apps/details… በስልክዎ በመጫን ቀጥታ የቴሌቪዥን ስርጭት፣ ኤፍኤም 98.1 እና ብሄራዊ ሬዲዮን ይከታተሉ፡፡ ቪዲዮዎችንም ይመልከቱ፡፡

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.