Fana: At a Speed of Life!

የሐይማኖት ተቋማት ጉባኤ በሱሉልታ ከተማ ለሚኖሩ አቅመ ደካማ ሴቶች ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 28፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ሐይማኖት ተቋማት ጉባኤ በሱሉልታ ከተማ ለሚኖሩ አቅመ ደካማ ሴቶች ድጋፍ አደረገ።

የጉባኤው ጠቅላይ ጸሐፊ ቀሲስ ታጋይ ታደለ በሱሉልታ ከተማ በመገኘት ድጋፉን አስረክበዋል።

ጉባኤው ድጋፉን ያደረገው ከኖርዌይ ቤተክርስቲያን ጋር በመተባበር መሆኑን ጠቅሰው፤ ድጋፉም በዋናነት የሴቶች ንጽሕና መጠበቂያ፣ ሳሙና እና ሳኒታይዘር ያካተተ መሆኑን ገልፀዋል።

ወቅቱ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ እየተስፋፋ ያለበት በመሆኑ በሽታውን ለመከላከልና በዋናነትም ሴቶችን ለማገዝ ያለመ ድጋፍ መሆኑን ተናግረዋል።

ድጋፉን የተረከቡት የተፈናቃዮቹ ተወካይ ወይዘሮ ፀሐይ ጌታሁን በበኩላቸው÷ እርዳታው የሴቶችን ችግር በማቃለል ረገድ በጎ ሚና እንዳለው መናገራቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

ጉባኤው ላደረገው ድጋፍ ምስጋና አቅርበው፤ ሌሎች ተቋማትም የጉባኤውን አርአያነት በመከተል ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል።

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.