Fana: At a Speed of Life!

የሕዝቡን አንገብጋቢ ችግር ለመፍታት ከመቸውም ጊዜ በላይ በቁርጠኝነት እንሰራለን – ከንቲባ አዳነች አቤቤ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 24፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሕዝቡን አንገብጋቢ ችግር ለመፍታት ከመቸውም ጊዜ በላይ በቁርጠኝነት እንሰራለን፤ ሰርተንም እናስረክባለን ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ተናገሩ፡፡
ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ በቂርቆስ ክፍለ ከተማ እየተገነቡ ያሉ የ60 ቀናት ሰው ተኮር ፕሮጀክቶችን ጎብኝተዋል፡፡
በጉብኝታቸው ወቅት እንደገለጹት÷ የሕዝቡን አንገብጋቢ ችግር ለመፍታት ከመቸውም ጊዜ በላይ በቁርጠኝነት እንሰራለን፤ ሰርተንም እናስረክባለን” ብለዋል፡፡
ከንቲባዋ ባደረጉት ጉብኝት÷ የሕዝብ አገልግሎት ዘርፎች፣ የከተማ ማስዋብና የከተማ ግብርና ሥራዎች ያሉበትን ደረጃ ተመልክተዋል።
በጉብኝታቸውም አብዛኞቹ ስራዎች በተያዘላቸው የጊዜ ገደብ እየተከናወኑ መሆናቸውን ገልፀው÷ ለሕዝባችን በገባነው ቃል መሰረት ሌሊትና ቀን ያለ ዕረፍት ሰርተን ለሕዝብ አገልግሎት እንዲውሉ በማድረግ ወደ ሌላ ሰው ተኮር ተግባራት እንሸጋገራለንም ነው ያሉት።
ግንባታዎችም ሆኑ ሌሎች ሰው ተኮር ተግባራት በተያዘላቸው የጊዜ ገደብ እንዳይጠናቀቁ እንቅፋት የሚሆኑ ማንኛውም ችግሮች ካሉ ከተማ አስተዳደሩ አስፈላጊውን ድጋፍ በማድረግ የሚፈቱበትን አግባብ ለማመቻቸት በተለየ ሁኔታ እየሠራ መሆኑንም ነው የገለጹት፡፡
እስካሁን ባለው ሂደትም ለበርካታ ችግሮችና የአሰራር ማነቆዎች መፍትሔ እየሰጡ መሆናቸውን ገልፀዋል።
ከፕሮጀክት ጉብኝቱ ጎን ለጎንም÷ በአገልግሎት ሰጭ ተቋማት ያለውን የሕዝብ አገልግሎት አሰጣጥ፣ በአገልግሎቱ ዘርፍ የሚታዩ ችግሮችን በወረዳዎች ተገኝተው መመልከታቸውን ከከንቲባ ጽሕፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.