Fana: At a Speed of Life!

የመምህራን ቀን ዓመታዊ በዓል አውደ ጥናት ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 20፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የመምህራን ቀንን “መምህራን ቀውስ ለመቀልበስም ሆነ ለመጭው ጊዜ ብሩህነት ግንባር ቀደም ሚና አላቸው” በሚል መሪ ቃል ትምህርት ሚኒስቴር ከባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ጋር በትብብር ያዘጋጁት አውደ ጥናት በባህር ዳር ተካሄደ።

የትምህርት ሚኒስትሩ ዶክተር ጌታሁን መኩሪያ በአውደ ጥናቱ ላይ አሁን እየታዩ ያሉ ሀገራዊ ችግሮችን ለመቅረፍ ግብረገብነት ያለው፣ ብዝሃነትንና አንድነትን የሚያስተናግድ ትውልድ ለማፍራት እንደሚሰራ አንስተዋል።

የመምህርነት ሙያ ከዘር፣ ከብሄርና ከወገንተኝነት ነፃ ሆኖ ከፍ ብሎ የሚገኝ ግዙፍ ሙያ ነው ያሉት ሚኒስትሩ ይህን እውን ለማድረግ መምህራን ትልቅ ኃላፊነት አለባቸው ብለዋል።

በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የአማራ ክልል የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪና የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ ሙሉነሽ አበበ ሁሉም የመምህራን የእጅ ስራ ውጤት መሆኑን አስታውሰዋል፡፡

ኃላፊዋ የመምህራን ክብር በሚከፈሉት ክፍያና በሚኖሩት ኑሮ የሚለካ ሳይሆን ሙያው በራሱ ክብር የሚሰጠው መሆኑንም ጠቅሰዋል።

የትምህርት ዘርፉ ለሀገር እንዲጠቅም ለማድረግም የመምህራንን ጥቅም ማስጠበቅ አስፈላጊ መሆኑንም ተናግረዋል።

የመምህራን ቀን በሁሉም ክልሎች በተለያዩ ዝግጅቶች እየተከበረ ሲሆን የማጠቃለያ ዝግጅቱ ደግሞ በአዲስ አበባ እንደሚደረግ ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.