Fana: At a Speed of Life!

የመረዳዳት ባህል ተጠናክሮ መቀጠል አለበት – ም/ጠ/ሚ ደመቀ መኮንን

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 15፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በረመዳን ወር ተጠናክሮ የቀጠለው የመረዳዳት ባህል ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን አሳሰቡ።

ምክትል  ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከካቢኔ አባላት ጋራ በመሆን ቫቲካን አካባቢ የሚገኘውን ቢላሎል ሀበሺ የልማትና መረዳጃ እድር ጎብኝተዋል።

በዚህ ወቅትም የመረዳዳት እርስ በርስ መተሳሰብ፣ መመካከር፣ መደጋገፍ ባህላችንን በማጠናከር ኮቪድ 19ና አምበጣ የፈጠሩትን ተግዳሮት መሻገር አለብን ብለዋል ፡፡

የሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ በበኩላቸው ባህላዊ የማህበራዊ መደጋገፍ ስራዎችን መንግስት በማጠናከር ትኩረት ሰጥቶ እንደሚሰራ ገልፀዋል።

ዶ/ር ኤርጎጌ እንደ እድር አይነት ባህላዊ የማህበራዊ መደጋገፊያ ተቋማት የሆኑትን በማጠናከር የመተጋገዝ ባህላችንን እናጠናክራለን ብለዋል።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩና የካቢኔ አባላት ቢላሎል ሀበሺ ለሚረዳቸው ወላጅ አልባና ለችግር የተጋለጡ ሰዎችን እንኳን ለ1 ሺህ 441ኛው የዒድ አልፈጥር በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን በማለት የአልባሳት የበግና የምግብ ልገሳ ማድረጋቸውን ከሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ቢላሎል ሀበሺ የልማትና መረዳጃ እድር ባለፉት 20 አመታት ከቀብር ባለፈ ከ4 ሺህ በላይ ወላጅ አልባና ለችግር የተጋለጡ ሰዎችን በትምህርትና ጤና ዘርፍ ላይ እየደገፈ ይገኛል፡፡

 

#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዘናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.