Fana: At a Speed of Life!

የመሰረተ ልማት ስራዎች በተያዘላቸው ጊዜ እንዲጠናቀቁ እየተሰራ ነው – አቶ አገኘሁ ተሻገር

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 3፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) በአማራ ክልል በፌዴራል መንግስት በጀት እየተገነቡ የሚገኙ የመሰረተ ልማት ስራዎች በተያዘላቸው ጊዜ እንዲጠናቀቁ የክልሉ መንግስት አስፈላጊውን ድጋፍ እያደረገ መሆኑን የክልሉ ርዕሰ መስተዳደር አገኘሁ ተሻገር ተናገሩ።

የክልልና የከተማ አስተዳደሩ የስራ ኃላፊዎች በባህርዳር ከተማ በፌዴራል መንግስት እየተገነቡ የሚገኙ የአባይ ድልድይና ከኤርፖርት መገንጠያ እስከ ዘጌ እየተገነባ ያለውን ኮንክሪት አስፓልት መንገድ ዛሬ ተዘዋውረው ተመልክተዋል።

ርዕሰ መስተዳደሩ በጉብኝቱ ላይ እንዳሉት በክልሉ ላለፉት በርካታ ዓመታት ያልተሰሩ የመንገድና መሰል መሰረተ ልማቶች ከለውጡ በኋላ እየተገነቡ ይገኛሉ።

እነዚህ ፕሮጀክቶች በተያዘላቸው ጊዜ እንዲጠናቀቁ በግንባታ ሂደት እያጋጠሙ ያሉ ችግሮችን ተከታትሎ መፍታት እንደሚገባ ተናግረዋል።

ለዚህም የክልሉ መንግስት አስፈላጊውን ድጋፍ እያደረገ መሆኑን ጠቅሰው፤ ህብረተሰቡም ልማቱ የራሱ መሆኑን በመገንዘበ አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርግ ጠይቀዋል።

ዛሬ የተጎበኘው ከባህር ዳር ኤርፖርት መገንጠያ እስከ ዘጌ 21 ነጥብ 8 ኪሎ ሜትር ኮንክሪት የአስፓልት መንገድ ግንባታ ከ3ኛ ወገን ነፃ ያለመሆንና በተቋራጩ የአቅም ማነስ የመጓተት ችግር እንዳለ መመልከታቸውን ገልፀው፤ “ያጋጠመው የወሰን ማስከበር ችግርም በቀጣይ ይፈታል” ብለዋል።

“የመንገዱ መገንባት ግራና ቀኝ የአትክልት፣ ፍራፍሬና የአበባ ልማት በስፋት የሚካሄድበት ስፍራ በመሆኑ ለኢኮኖሚ ዕድገቱ መፋጠን የጎላ ድርሻ አለው” ብለዋል።

መንገዱ ተገንብቶ ሲጠናቀቅም በግብርና፣ በሪል ስቴት ግንባታ፣ በማኑፋክቸሪንግና ተያያዥ ልማቶች አካባቢውን ትልቅ የዕድገት ኮሪደር እንደሚያደርገው ገልጸዋል።

እንዲሁም በከፍተኛ ወጭ በአባይ ወንዝ ላይ እየተገነባ ያለው ተለዋጭ ድልድይ በተያዘለት ጊዜ እንዲጠናቀቅ ተቋራጩ ሌት ተቀን እየሰራ መሆኑን እንደተመለከቱ ተናግዋል።

የድልድዩ ግንባታ በ2014 መጨረሻ ሲጠናቀቅ የከተማዋን ዕድገት ከማፋጠን ባለፈ የትራፊክ ፍሰቱን በማሳለጥ ለቱሪዝም እድገት የጎላ አስተዋጽዖ እንደሚኖረውም መግለጻቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.