Fana: At a Speed of Life!

የመሰረተ ልማቶችን ጥራትና ተደራሽነት በማረጋገጥ ጠንካራ ሥርዓት እና አገር እንገነባለን- የኦሮሚያ ክልል መንግስት

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 19፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የመሠረተ ልማቶችን ጥራትና ተደራሽነት በማረጋገጥ ጠንካራ ሥርዓት እና አገር እንገነባለን ሲል የኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ገለጸ፡፡
 
የኦሮሚያ ክልል መንግስት በዛሬው ዕለት ባወጣው መግለጫ÷ በተያዘው ዓመት ማህበረሰቡን ተጠቃሚ የሚያደርጉ የተለያዩ መሰረት ልማቶችን መገንባት ላይ ትኩረት ተደርጎ እየተሰራ መሆኑን አስታውቋል፡፡
 
ለአብነትም በበጀት ዓመቱ ከተሰሩ ዋና ዋና የልማት ፕሮጀክቶች መካከል ትምህርት ቤቶች፣ ድልድዮች፣ የኤሌክትሪክ መስመሮች፣ መንገዶች፣ የንጹህ መጠጥ ውሃ፣ ሆስፒታሎች፣ ጤና ኬላዎች፣ መስኖ፣ የጎርፍ ማስወገጃዎች እና ሌሎችም እንደሚገኙበት በመግለጫው ተመላክቷል፡፡
 
ለእነዚህ የልማት ፕሮጀክቶች ግንባታም 42 ቢሊየን 650 ሚሊየን 473 ሺህ ብር በላይ ወጪ መደረጉ ነው የተገለጸው፡፡
 
ግንባታቸው የተጠናቀቁ የልማት ፕሮጄክቶችም በክልል እና በወረዳ ደረጃ ከሰኔ 20 እስከ ሰኔ 30 ቀን 2014 ዓ.ም ተመርቀው ለህዝብ አገልግሎት ክፍት እንደሚደረጉ መጠቆሙን ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
 
ክልሉ የተፈጠሩ ሰው ሰራሽ እና ተፈጥሯዊ ችግሮችን በመቋቋም የተጀመሩ ፕሮጀክቶች በስኬት የማጠናቀቁ ተሞክሮም በቀጣይ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበትም ተመላክቷል፡፡
 
የክልሉ ህዝብም የተሰሩ መሰረተ ልማቶችን በጥንቃቄ በመገልገል እና በመጠበቅ ረገድ የበኩሉን ሚና እንዲወጣ ጥሪ ቀርቧል።
 
 
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
 
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.