Fana: At a Speed of Life!

የመስቀል አደባባይ ፕሮጀክት ዛሬ ይመረቃል

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 6፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በ2 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር በላይ የተገነባው የመስቀል አደባባይ ፕሮጀክት ዛሬ ይመረቃል።

ፕሮጀክቱ የቀድሞ ያለውን ስፍራ ይዘቱን ሳይቀይር ሁለት የግንባታ አካል ወደ ውስጥ በመግባት የመኪና ማቆሚያ እንዲሁም አደባባዩንና ጎዳናዎችን የማስዋብ ሥራ ነው የተሰራው፡፡
ከዚህ ቀደም ሲሰጥ የነበረውን ሃይማኖታዊ ፣ህዝባዊ እና ሌሎች ማህበራዊ ዝግጅቶች በተለይ በከተማዋ ብዙኃንን ታሳቢ ያደረጉ ኩነቶችን በተሻለ እና ምቹ በሆነ መልኩ አገልግሎት ለመስጠት በሚያስችል መልኩ የተገነባ ነው፡፡
በሰኔ 2012 ዓ.ም የተጀመረው ይህ የመስቀል አደባባይ ፕሮጀክት ለግንባታ ስራው በ2 ቢሊየን 589 ሚሊየን 800 ብር በጀት መጠናቀቁን ከአዲስ አበባ ከተማ ፕሬስ ሴክሬታሪያት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.