Fana: At a Speed of Life!

የመቐለ ከተማ ጊዜያዊ አስተዳደር ከንግዱ ማህበረሰብ ጋር ተወያየ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 13፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የመቐለ ከተማ ጊዜያዊ አስተዳደር በከተማዋ ከሚገኙ የንግዱ ማህበረሰብ ጋር በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት አካሂዷል፡፡

በመቐለ ከተማ የሚገኙ የንግድ ማህበረሰብ አባላት በከተማዋ የተፈጠረውን ሰላማዊ እንቅስቃሴ በመጠቀም ወደ ስራቸው በሙሉ አቅም እንዲመለሱ ጥሪ ቀርቧል፡፡

በውይይቱ ላይ የተሳተፉ ነጋዴዎች የንግድ ስራቸው ከባንክ ጋር የተሳሰረ በመሆኑ የባንክ አገልግሎት እንዲጀመርላቸው ጠይቀዋል፡፡

በክልሉ ከቀበሌ ጀምሮ እስከ ላይኛው እርከን ያለ የመንግስት መዋቅርም ፈጥኖ ወደ ስራ እንዲገባና ነጋዴዎቹ ወደ ንግድ ስራቸው በሙሉ አቅም ለመመለስ የከተማው ፖሊሶች በአፋጣኝ ስራ እንዲጀምሩም ጠይቀዋል፡፡

በከተማዋ አሁን የሚታየውን የኑሮ ውድነት ችግርም መንግስት ከንግዱ ማህበረሰብ ጋር በመሆን ሊፈታው ይገባል ብለዋል።

በተለይ መሰረታዊ ሸቀጦችን የሚያቀርቡ ነጋዴዎች የዋጋ ጭማሪ ከማድረግ እንዲቆጠቡም ተናግረዋል።

የመቐለ ከተማ ጊዜያዊ አስተዳደር ከንቲባ አቶ አታክልቲ ሃይለስላሴ፤ ውይይቱ ያስፈለገው በከተማው ነጋዴው ወደ ስራ እንዳይገባ ያጋጠሙትን ችግሮች በመረዳት እና በማቃለል ወደ ስራቸው እንዲገቡ ለማስቻል ነው ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.