Fana: At a Speed of Life!

የመተከል ተፈናቃዮች በቂ ሰብዓዊ ድጋፍ እንዲደረግላቸውና የጸጥታ ስጋት እንዳይገጥማቸው እየተሠራ ነው – የተፈናቃዮች አስመላሽ ግብረ ኀይል

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 18 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ከመተከል ዞን ተፈናቅለው የቆዩ ዜጎችን ወደ ቀያቸው በመመለስ የማቋቋም ሥራ እየተከናወነ ነው፡፡

ተፈናቃዮቹ ወደ ማንዱራ፣ ድባጤ፣ ቡለንና ዳንጉር ወረዳዎች በመመለስ በአንድ ማዕከል ለጊዜው እንዲቆዩ እንደሚደረግ የተፈናቃዮች አስመላሽ የቴክኒክ ግብረኀይል አባል በትግሉ ተስፋዬ አስረድተዋል፡፡

ተፈናቃዮቹን በማስመለሱ ሂደት ውስጥ ከመተከል ዞን የተፈናቀሉ ዜጎችን ብቻ ሳይሆን ከግልገል በለስ የተፈናቀሉ ዜጎችንም ወደ ቀያቸው የመመለስ ሥራ እንደሚከናወን አቶ በትግሉ ተናግረዋል፡፡

ተፈናቃዮቹ ዘለቄታዊ የሆነ ሕይወት መኖር እስከሚጀምሩ ድረስ በአንድ ማዕከል እንዲቆዩ ይደረጋል ያሉት አቶ በትግሉ ተፈናቃዮች በቂ ሰብዓዊ ድጋፍ እንደሚደረግላቸውና ምንም አይነት የጸጥታ ስጋት እንዳይገጥማቸው እየተሠራ ነው ብለዋል፡፡

ለተፈናቃዮቹ የጋራ የእርሻ መሬት መዘጋጀቱን ና ግብዓት ለማቅረብም እየተመቻቸ ነው ማለታቸውን አሚኮ ዘግቧል፡፡

በቀጣይ ከማኅበረሰቡ ጋር የእርቀ ሰላም ጉባዔ እንደሚደረግም ገልጸዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.