Fana: At a Speed of Life!

የመንግስት የልማት ድርጅቶች የግማሽ ዓመት ሥራ አፈፃፀም እየተገመገመ ነው

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 8 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የሃገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ መርሃ ግብር ዋና አካል የሆነው የመንግስት የልማት ድርጅቶችን ውጤታማነት ለማሻሻል ፣ ተወዳዳሪነታቸውን ለማጎልበት እና የአገልግሎቶት አሰጣጣቸውን ቀልጣፋ እንዲሆኑ ለመደገፍ ያተኮረ ለአምስት ቀናት የሚቆይ ውይይት ተጀመረ፡፡

በመንግስት የልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር ኤጀንሲ ስር በትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ፣ በግብርና እና ግብርና መቀነበባር፣ በአምራች ኢንዱስትሪ እና ኢንጅነሪንግ፣ የንግድ እና የአገልግሎት ዘርፍ፣ የፋይናንስ ተቋማት፣ የተግባቦትና ግንባታ ስር ተመድበው የሚገኙ የመንግስት የልማት ድርጅቶች በ2013 በጀት አመት በመጀመሪያው አጋማሽ የነበራቸውን የስራ አፈጻጸም ግምገማ እየተካሄደ ይገኛል፡፡

ለሁሉም የልማት ድርጅቶች የኦዲት ሪፖርት ላይ የተሰጡ የማሻሻያ ሀሳቦችን ተግባራዊንት እንዲያረጋግጡ የግምገማው ትከረት ሰጥቷል፡፡

የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴመንግሰት የልማት ድርጅቶቹን ለመደገፍ የቴክኒክ ኮሚቴዎቸን አዋቅሮ ሲሰራ መቆየቱን አስታውሰው በተለይም ሁሉም የልማት ድርጅቶች ዓለም አቀፍ የፋይናንስ አስተዳደር እና ሂሳብ አያያዝ ስርዓት ተከትለው እንዲተገብሩ በመደረጉ የአሰራር መሻሻሎች እየተገኙ እንደሆነ ጠቅሰዋል፡፡

ሚኒስትሩ የመንግስት የልማት ድርጅቶችን የዕዳ መጠን ዘርዝሮ በማጥናትና የመክፈል አቅማቸውን ከግምት ውስጥ በማስገባት የመንግሥት የልማት ድርጅቶችን የዕዳ ጫና በማቃለል እና ውጤታማ ሆነው እንዲዘልቁ ለማስቻል የሚያግዝ የእዳና ሀብት አስተዳደር ኮርፖሬሽን እንዲቋቋም በሚኒስትሮች ምክር ቤት ተወስኖ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑንም አስገንዝበዋል፡፡

የመንግስት የልማት ድርጅቶች ለሀገር ልማትና እድገት የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እንዲያበረክቱ መንግስት የተለያዩ የፖሊሲ ማሻሻያዎች በመቅረፅ እና የአሰራር ስርዓቶችን በመንደፍ ተግባራዊ እያደረገ እንደሚገኝ አብራርተዋል፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት መተግበሪያን https://play.google.com/store/apps/details?id=com.companyname.FanaAm በስልክዎ በመጫን ቀጥታ የቴሌቪዥን ስርጭት፣ ኤፍኤም 98.1 እና ብሄራዊ ሬዲዮን ይከታተሉ፡፡ ቪዲዮዎችንም ይመልከቱ፡፡

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.