Fana: At a Speed of Life!

የመን በዓለም አስካፊው የሰብአዊ ቀውስ ተጋርጦባታል

አዲስ አበባ፣ የካቲት 3፣ 2012(ኤፍ ቢ ሲ) በዓለም አስከፊው እና ከባዱ የሰብዓዊ ቀውስ የመን ላይ መጋረጡ ተነገረ፡፡

በዓለም ላይ ዋና ድጋፍ አድራጊ እና የረድኤት ኤጀንሲዎች በብራሰልስ አደጋ ለተጋረጠባቸው የመናዊያን ድጋፍ ለማሰባሰብ ውይይት እንደሚያደርጉ ተጠቁሟል።

በሚሊየን የሚቆጠሩ የመናዊያን  ህይወትም በእነዚህ ድጋፍ ሰጪ ተቋማት እጅ ላይ እንደሚገኝ ነው የተነገረው።

በቅርቡ የተባበሩት መንግስታት የፀጥታው ምክር ቤት ባወጣው መግለጫ በሀገሪቱ ያለው ችግር በተለይ የአገልግሎት ውስንነት ድጋፍ የሚያስፈልጋቸው 6 ነጥብ 7 ሚሊየን የመናውያን ላይ ተፅዕኖ እንዳለው ተጠቁሟል ፡፡

ሰብአዊ እርዳታ ሰጭ ኤጀንሲዎች የሰብአዊ መርሆዎችን ማክበር በሚችሉበት አካባቢ መሥራት እንዳለባቸው በየመን የተባበሩት መንግስታት የሰብዓዊ አስተባባሪ የሆኑት ሊሴ ግራንዴ ተናግረዋል ፡፡

በየመን እየተከሰተ ላለው ከባድ የሰብዓዊ ቀውስ በርካቶቹ የሃውቲ አማፂያንን ተጠያቂ በማድረግ ላይ ይገኛሉ።

ምንጭ፡- ቢቢሲ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.