Fana: At a Speed of Life!

የመከላከያ ፋውንዴሽን ለሰራዊቱ አባላት ያስገነባቸውን የመኖሪያ አፓርትመንቶች የዕጣ ማውጣት መርሐ ግብር ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 11፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢፌዴሪ የመከላከያ ፋውንዴሽን ለሰራዊቱ አመራርና አባላቶች ያስገነባውን የመኖሪያ አፓርትመንቶች የዕጣ ማውጣት መርሐ ግብር ተካሂዷል።

በመርሃ ግብሩ ላይ የመከላከያ ሚኒስትር ዶክተር አብርሃም በላይን ጨምሮ ከፍተኛ የሰራዊቱ አመራሮች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

የመከላከያ ሚኒስትሩ ዶክተር አብርሀም በላይ ሀገርን በመስዋዕትነቱ እያስከበረ የሚገኘው ጀግናው መከላከያ ሰራዊት ተጠቃሚ ለማድረግ አዳዲስ አሰራሮችን በመዘርጋት ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ እንደሚገኝ ገልፀዋል፡፡

የመከላከያ ሰራዊት ፋውንዴሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ ሜጀር ጄኔራል ኩምሳ ሻንቆ በበኩላቸው ፋውንዴሽኑ በኢንዱስትሪና በእርሻ ከመሰማራቱ በተጨማሪ በተለያዩ የሀገራችን ከተሞች ውስጥ በስምንት ሳይቶች የጋራ መኖሪያ ቤቶችን በመገንባት የሰራዊቱን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በርካታ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን ተናግረዋል።

በዕለቱ በመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ተገንብተው የተጠናቀቁ 528 ቤቶች ዕጣ የወጣባቸው መሆኑን ከመከላከያ ሰራዊት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.