Fana: At a Speed of Life!

የመከላከያ ሰላም ማስከበር ማዕከል ዓለም አቀፍ ሰላም ማስከበር ማሰልጠኛ ተቋም ከምስራቅ አፍሪካ ተጠንቀቅ ኃይል ጋር በጋራ በሚሰሩባቸው ጉዳዮች ላይ ተፈራረሙ

አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 19 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የመከላከያ ሰላም ማስከበር ማዕከል ዓለም አቀፍ ሰላም ማስከበር ማሰልጠኛ ተቋም እና የምስራቅ አፍሪካ ተጠንቀቅ ኃይል በስልጠና፣ በምርምር እና በአቅም ግንባታ ስራዎች ላይ በጋራ ለመስራት ተስማሙ፡፡
በስምምነቱ ኢትዮጵያ በተባበሩት መንግስታት እና በአፍሪካ ህብረት በዓለም አቀፍ ሰላም ማስከበር ተልዕኮ ያከናወነቻቸውን ውጤታማ ግዳጆች፣ የማሰልጠኛ ተቋሙ ተልዕኮ እና የተሰሩ ስራዎች እንዲሁም የትምህርት አሰጣጡን የተመለከተ ገለፃ ተደርጓል፡፡
በመከላከያ ሰላም ማስከበር ማዕከል የዓለም አቀፍ ሰላም ማስከበር ማሰልጠኛ ተቋም አዛዥ ብርጋዴር ጄኔራል ሰብስቤ ዱባ÷ ማሰልጠኛ ተቋሙ ሰላም ለማስከበር ለሚሰማሩ ለመከላከያ ሰራዊት፣ ለፖሊስና ለሲቪል አባላት ቅድመ ስምሪት ስልጠናዎች በተጠናከረ መልኩ እየሰጠ ይገኛል ብለዋል።
ስምምነቱ ስራዎችን በተሻለ መልኩ ለመስራት አወንታዊ ፋይዳው የጎላ መሆኑን ገልፀው÷በቀጣይም የትብብር ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ አመላክተዋል፡፡
የምስራቅ አፍሪካ ተጠባባቂ ኃይል ዳይሬክተር ብርጋዴር ጄኔራል ጌታቸው ሺፈራው በበኩላቸው÷ በምስራቅ አፍሪካ ያሉ የሰላም ማስከበር ስልጠና ተቋሞች የምስራቅ አፍሪካን ተጠንቀቅ ኃይል ስልጠናና ድጋፍ የመስጠት ኃላፊነት እንዳለባቸው አንስተዋል፡፡
ዳይሬክተሩ ከመከላከያ ሰላም ማስከበር ማዕከል የዓለም አቀፍ ሰላም ማስከበር ማሰልጠኛ ተቋም ጋር በጋራ በመስራት የአቅም ግንባታ ስራዎቻችንን አጠናክረን እንቀጥላለን ማለታቸውን ከመከላከያ ሰራዊት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.