Fana: At a Speed of Life!

የመከላከያ ሰራዊት ሒዋነ ከተማን ከጁንታው እጅ ማስለቀቁን ሌተናል ጄኔራል ባጫ ደበሌ ተናገሩ

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 18 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የመከላከያ ሰራዊቱ የራያ ግንባር ሒዋነ ከተማን ከጁንታው እጅ ማስለቀቁን ሌተናል ጄኔራል ባጫ ደበሌ ተናገሩ፡፡
ሌተናል ጄኔራል ባጫ ደበሌ ዛሬ በሰጡት መግለጫ አሁን ላይ የጁንታው ቡድን ወደ ዐዲ ጉደም መሸሹን ተናግረዋል፡፡
ሰራዊቱ አካባቢውን በተቆጣጠረበት ወቅት የጥፋት ሃይሉ ይጠቀምባቸው የነበሩ 6 ታንክ እና ሁለት ዙ23ን ጨምሮ በርካታ መሳሪያዎች መደምሰሳቸውንም ነው የተናገሩት፡፡
መከላከያ ሰራዊቱ አስቸጋሪ መልክዓ ምድሩን በብቃት በማለፍ የጁንታውን ቡድን መደምሰሱንም አስረድተዋል፡፡
ከዚህ ባለፈም ሰራዊቱ የጥፋት ሃይሉ ሲሸሽ ያወደማቸውን ድልድዮችና መሰረተ ልማቶች እየጠገነ በጁንታው ቡድን ላይ ድል ማስመዝገቡንም አውስተዋል፡፡
አሁን ላይ ሰራዊቱም ወደ መቐለ የሚያደርገውን ግስጋሴ መቀጠሉን ጠቅሰው ሰራዊቱ ከተማዋን በአጭር ጊዜ እንደሚቆጣጠርም ገልጸዋል፡፡
በፋሲካው ታደሰ
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.