Fana: At a Speed of Life!

የመውሊድ በዓል በጅማ ከተማ በደማቅ ሁኔታ ተከበረ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 8፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) 1 ሺህ 496ኛው ጠመውሊድ በዓል በጅማ ከተማ መድረሰቱል ኸይርያ ትምህርት ቤትየተለያዩ የእምነቱ ተከታዮች እና የሌሎች እምነት ተከታዮች በተገኙበት በድምቀት ተከብሯል፡፡
በዓሉ ከማለዳው ጀምሮ በዱአ እና ነብዩን በሚያወድሱ መንዙማዎች ነው የተከረው።
በ1958 ዓ.ም. የተቋቋመው መድረሳ ትምህርት ቤት የእስልምና ትምህርቶችን ጨምሮ ዘመናዊ ትምህርትን በመስጠት ብዙ ምሁራንን ያፈራ መሆኑ ተገልጿል፡፡
በጅማ ሙኒር መስጂድ ኢማም የሆኑት ሼክ መሀመድ አባዲጋ እንደተናገሩት÷ የነብዩ መወለድ ለአለም ብርሀን እንደሆነ ሁሉ ህዝበ ሙስሊሙም ለሀገር አንድነት እና በመረዳዳት ቀኑን ማሳለፍ አለበት ብለዋል።
በአብዱረህማን መሀመድ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.