Fana: At a Speed of Life!

የመዲናዋ ሴት የምክር ቤት አባላት በሚቀጥሉት ዓመታት የተሻለ ስራ መስራት ይኖርብናል- ከንቲባ አዳነች አቤቤ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 13፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በዛሬው እለት የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት 3ኛ ዙር የምርጫ ዘመን የሴት ምክር ቤት አባላት ኮከስ ምስረታ ጠቅላላ ጉባኤ ተካሂዷል፡፡

በዚሁ ወቅት ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ “መደራጀት ሃይል ነው፤ ግን መደራጀት በራሱ ግብ አይደለም” ብለዋል፡፡

“ስለሆነም ስንደራጅ በሚቀጠርና በሚዳሰስ ስራዎች ማጀብ ይኖርብናል” ሲሉ ገልፀዋል፡፡

በቀረው አራት አመት ለሚቀጥሉት የሴት ምክር ቤት አባላት ከጥቃቅን አጀንዳዎች ይልቅ ዋና አላማ ላይ በማተኮር የተሻለ ነገር በመፍጠር መስራት እንደሚገባም አስገንዝበዋል።

ሴቶች ጋር ያለምንም ማጋነን ፤የተለየ ርህራሄ፤ ችሎታ ፤ተሰጥኦ እናትነት አለ ያሉት ከንቲባዋ፤ ይህ ከትምህርት ጋር ሲዳብር ደግሞ ትልቅ ውጤት የሚያመጣ በመሆኑ በሚገባ በማስተባበር ለፍሬ ማድረስ የኮከሱ ትልቅ ተልዕኮ መሆኑን አስምረውበታል፡፡

የአዲስ አበባ ምክር ቤት አፈጉባኤ ወይዘሮ ቡዜና አልቃድር፤ የሴቶችን ተሳትፎ ውስንነት ከፍ ለማድረግ ለውጡ ለሴቶች የፈጠረውን መልካም እድል በመጠቀም ከቃል ባለፈ ለከተማዋ ብልፅግና መስራት እንደሚገባ መናገራቸውን የከንቲባ ጽህፈት ቤት መረጃ ያመላክታል።

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.