Fana: At a Speed of Life!

የመገናኛ ብዙሃን ሙስናን በመከላከል እና በሥነ ምግባር ግንባታ ተቀዳሚ ሚናቸውን እንዲወጡ ተጠየቀ

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 26 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የመገናኛ ብዙሃን ሙስናን በመከላከል እና በሥነ ምግባር ግንባታ ቀዳሚ ተዋናይ እንዲሆኑ የፌደራል የሥነ ምግባር እና የፀረ- ሙስና ኮሚሽን ጥሪ አቀረበ።

ኮሚሽኑ “ሥነ ምግባርን በመገንባት እና ሙስናን በመከላከል ረገድ የሚዲያ ተቋሟት ሚና” በሚል የውይይት መድረክ አካሂዷል፡፡
በመድርኩ ላይ የመገናኛ ብዙሃን አመራሮች እና ባለሞያዎች ተሳታፊ የሆኑ ሲሆን ÷ ሙስና በአለም አቀፍ ደርጃ እና በኢትዮጵያ ያለውን ሁኔታ የተመለከተ፣ ሙስናን እና የመገናኛ ብዙሃን ሚና እንዲሁም የ10 አመት የሙስና መከላከል እቅድ ቀርቧል።
የቀርበውን ጽሁፍ መነሻ በማድረግም የተለያዩ ሃሳቦች ተነስተዋል፡፡
እንዲሁም ሚዲያው ነጻና ገለልተኛ ሆኖ እንዳይሰራ የተለያዩ ጫናዎች መኖራቸው በመድረኩ ተገልጿል፡፡
ይሁንእንጂ ጫናውን ተቋቁሞም ቢሆን ሙስናን ለመከለክል የሚያስችሉ ተግባራትን መከወን እንደሚገባም ተነስቷል።
ተሳታፊዎቹ በበኩላቸው ሙስናን ለመከላከል ህዝቡ ጋር ወርዶ መስራት ተገቢ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡
በአዳነች አበበ

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳ
የፋና ድረ ቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.