Fana: At a Speed of Life!

የመጋቢት ወር የዋጋ ግሽበት 20 ነጥብ 6 በመቶ ሆኖ መመዝገቡ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 28፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የመጋቢት ወር የዋጋ ግሽበት 20 ነጥብ 6 በመቶ ሆኖ መመዝገቡን የማዕከላዊ ስታትስቲክስ ኤጀንሲ አስታወቀ፡፡

ኤጀንሲው በእህሎች ላይ የታየው የዋጋ ጭማሪ በያዝነው ወርም የቀጠለ መሆኑን ጠቅሶ ለምግብ ዋጋ ግሽበት መጨመር ከፍተኛ አስተዋጽዖ ማድረጋቸውንም ነው ያስታወቀው፡፡

የመጋቢት ወር የምግብ ዋጋ ግሽበት ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር በ22 በመቶ ጭማሪ ማሳየቱንም ገልጿል።

በተጨማሪም አትክልትና ጥራጥሬ ዓይነቶች የዋጋ ጭማሪ አሳይተዋል፡፡

በሌላ በኩል የምግብ ዘይት፣ ቅመማ ቅመም በርበሬ፣ ፍራፍሬ፣ አትክልት፣ ድንችና ቡና የዋጋ ጭማሪ በዚህ ወርም በመቀጠሉ ለዋጋ ግሽበት ምጣኔ መጨመር አስተዋጽዖ አድርገዋል።

ምግብ ነክ ያልሆኑ የዋጋ ግሽበት የመጋቢት ወር 2013 ዓ.ም ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር የ18 ነጥብ 9 በመቶ ጭማሪ በማሳየት ፈጣን ዕድገት አሳይቷል፡፡

ይህም ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር ከፍ እንዲል ካደረጉት ዋነኛ ምክንያቶች ውስጥ በተለይም በአልኮልና ትምባሆ፣ ልብስና ጫማ፣ አነቃቂዎች፣ የቤት እንክብካቤና ኢነርጅ (ማገዶና ከሰል)፣ የቤት መስሪያ እቃዎች (ሲሚንቶና የቤት ክዳን ቆርቆሮ)፣ ህክምና፣ ትራንስፖርት (ነዳጅ) እና ጌጣጌጥ (ወርቅ) ላይ የታየው የዋጋ ጭማሪ መሆኑ ነው የተጠቀሰው፡፡

አጠቃላይ የዋጋ ግሽበት ካለፈው ወር ጋር ሲነጻፀር በ2 ነጥብ 9 ከመቶ ጭማሪ ማሳየቱን ኢዜአ ኤጀንሲውን ጠቅሶ ዘግቧል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.