Fana: At a Speed of Life!

የመጨረሻዎቹ የዴሞክራሲ ገንቢ እና ጠባቂዎች ራሳችን ኢትዮጵያውያን እንጂ ወዳጆቻችን አይደሉም -ጠ/ሚ ዐቢይ  አሕመድ

አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 26 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠ/ሚ ዐቢይ ከክልል ፕሬዚዳንቶችና ከምርጫ ቦርድ አመራሮች ጋር  ሳምንታዊ የምርጫ ቅድመ ዝግጅትን ገምግመዋል።

በውይይቱም  የመራጮች ምዝገባ በጥሩ ሁኔታ እየተካሄደ  መሆኑ ተብራርቷል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ የትስስር ገጻቸው ላይ ÷ እስካሁን ያልተመዘገባችሁ ዜጎች በተራዘመው የምዝገባ ጊዜ ተጠቅማችሁ የምርጫ ካርድ እንድትወስዱ አበረታታለሁ ብለዋል ።

በምርጫ ጣቢያዎች የጸጥታ አካላት ምደባ እየተካሄደ ሲሆን፣ በቀጣይ ሳምንታት የሚሰማሩ ይሆናልም ነው ያሉት ።

የመጨረሻዎቹ የዴሞክራሲ ገንቢ እና ጠባቂዎች ራሳችን ኢትዮጵያውያን እንጂ ወዳጆቻችን አይደሉም ብለዋል።

ባለቤት ይወስናል፤ ወዳጅ ደግሞ  ያግዛል። የምርጫው ሂደት ስኬታማ እና ሰላማዊ እንዲሆን በጋራ እንሥራ ብለዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.