Fana: At a Speed of Life!

የሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ የሲሚንቶ አቅርቦቱ እንዲጨምር ይሰራል- ኢ/ር ታከለ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 15 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ በሙሉ አቅሙ እንዲጠቀምና የሲሚንቶ አቅርቦቱ እንዲጨምር እንደሚሰራ የማዕድን እና የነዳጅ ሚኒስትር ኢንጅነር ታከለ ገለፁ።

ሚኒስትሩ በዛሬው እለት ከኬሚካል ኢንዱስትሪዎች ኮርፓሬሽን የቦርድ አባላት ጋር በጋራ በመሆን የሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካን ጎብኝተዋል።

ፋብሪካው ያለበት ቦታ ለሲሚንቶ ግብአት መሆን የሚችል የተፈጥሮ ሀብት በብዛት የሚገኝበት ቢሆንም ፋብሪካው የሚያመርተው ምርት ግን  ይህንን የሚመጥን አይደለም ብለዋል።

በመሆኑም  ፋብሪካው በሙሉ አቅሙ እንዲጠቀምና የሲሚንቶ አቅርቦቱ እንዲጨምር እንደሚሰራ ነው የተናገሩት።

ፋብሪካው በሲሚንቶ ገበያው ላይ ላይ ያለው ተሳትፎ 25 በመቶ ብቻ ነው ያሉት ሚኒስትሩ የፋብሪካውን ምርትና ተደራሽነት በማስፋትም ይህ የገበያ ድርሻ ከፍ እንዲል ድጋፍ ይደረጋልም ብለዋል።

እንዲሁም የገበያ ትስስሩን ማጠንከር ላይ በትኩረት እንደሚሰራም አስታውቀዋል።

ፋብሪካው የሚያመርተውን ምርት በዝቅተኛ ዋጋ የሚያቀርብ ቢሆንም ገበያ ላይ በእጥፍ እየተሸጠ ተብሏል

ይህንን ማስተካከልም ትልቁ ስራ  እንደሚሆን የተናገሩት ሚኒስትሩ በአጠቃላይ ሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካን ታሪኩንና አቅሙን በሚመጥን መልኩ ለማሳደግ እንደሚሰራ ገልፀዋል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.